ዘፍጥረት 21:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ሣራም ግብፃዊቷ አጋር ለአብርሃም የወለደችለት ልጅ+ በይስሐቅ ላይ እንደሚያፌዝበት+ በተደጋጋሚ አስተዋለች። ዘፀአት 1:13, 14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 በመሆኑም ግብፃውያን እስራኤላውያንን ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ በባርነት ይገዟቸው ጀመር።+ 14 የሸክላ ጭቃ በማስቦካት፣ ጡብ በማሠራትና በእርሻ ላይ ማንኛውንም ዓይነት የባርነት ሥራ እንዲሠሩ በማድረግ ሕይወታቸውን መራራ አደረጉባቸው። አዎ፣ ማንኛውንም ዓይነት የባርነት ሥራ በማሠራት በጭካኔ ያንገላቷቸው ነበር።+ ዘፀአት 3:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለው፦ “በግብፅ የሚኖረውን የሕዝቤን መከራ በእርግጥ አይቻለሁ፤ አስገድደው በሚያሠሯቸው ሰዎች የተነሳ የሚያሰሙትን ጩኸት ሰምቻለሁ፤ እየደረሰባቸው ያለውንም ሥቃይ በሚገባ አውቃለሁ።+ የሐዋርያት ሥራ 7:6, 7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ከዚህም በላይ አምላክ፣ ዘሮቹ በሰው አገር ባዕዳን ሆነው እንደሚኖሩ እንዲሁም የአገሩ ሰዎች ለ400 ዓመት በባርነት እንደሚገዟቸውና እንደሚያጎሳቁሏቸው* ነገረው።+ 7 ደግሞም አምላክ ‘በባርነት የሚገዛቸውን ብሔር እፈርድበታለሁ፤+ ከዚያም በኋላ ከነበሩበት አገር ወጥተው በዚህ ስፍራ ቅዱስ አገልግሎት ያቀርቡልኛል’ ሲል ተናግሯል።+
13 በመሆኑም ግብፃውያን እስራኤላውያንን ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ በባርነት ይገዟቸው ጀመር።+ 14 የሸክላ ጭቃ በማስቦካት፣ ጡብ በማሠራትና በእርሻ ላይ ማንኛውንም ዓይነት የባርነት ሥራ እንዲሠሩ በማድረግ ሕይወታቸውን መራራ አደረጉባቸው። አዎ፣ ማንኛውንም ዓይነት የባርነት ሥራ በማሠራት በጭካኔ ያንገላቷቸው ነበር።+
7 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለው፦ “በግብፅ የሚኖረውን የሕዝቤን መከራ በእርግጥ አይቻለሁ፤ አስገድደው በሚያሠሯቸው ሰዎች የተነሳ የሚያሰሙትን ጩኸት ሰምቻለሁ፤ እየደረሰባቸው ያለውንም ሥቃይ በሚገባ አውቃለሁ።+
6 ከዚህም በላይ አምላክ፣ ዘሮቹ በሰው አገር ባዕዳን ሆነው እንደሚኖሩ እንዲሁም የአገሩ ሰዎች ለ400 ዓመት በባርነት እንደሚገዟቸውና እንደሚያጎሳቁሏቸው* ነገረው።+ 7 ደግሞም አምላክ ‘በባርነት የሚገዛቸውን ብሔር እፈርድበታለሁ፤+ ከዚያም በኋላ ከነበሩበት አገር ወጥተው በዚህ ስፍራ ቅዱስ አገልግሎት ያቀርቡልኛል’ ሲል ተናግሯል።+