ዕብራውያን 11:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 ሣራም የተስፋን ቃል የሰጠው እሱ ታማኝ* እንደሆነ አድርጋ ስላሰበች ዕድሜዋ ካለፈ በኋላም እንኳ ዘር ለመፀነስ በእምነት ኃይል አገኘች።+ 1 ጴጥሮስ 3:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ሣራም አብርሃምን ጌታዬ እያለች በመጥራት ትታዘዘው ነበር።+ እናንተም መልካም ማድረጋችሁን ከቀጠላችሁና በፍርሃት ካልተሸነፋችሁ+ ልጆቿ ናችሁ።