ዘፍጥረት 3:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 ከመሬት ስለተገኘህ+ ወደ መሬት እስክትመለስ ድረስ ላብህን እያንጠፈጠፍክ ምግብ ትበላለህ። አፈር ስለሆንክ ወደ አፈር ትመለሳለህ።”+ መዝሙር 146:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 መንፈሱ* ትወጣለች፤ ወደ መሬት ይመለሳል፤+በዚያው ቀን ሐሳቡ ሁሉ ይጠፋል።+ መክብብ 9:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ሕያዋን እንደሚሞቱ ያውቃሉና፤+ ሙታን ግን ምንም አያውቁም፤+ ከእንግዲህም የሚያገኙት ብድራት* የለም፤ ምክንያቱም የሚታወሱበት ነገር ሁሉ ተረስቷል።+ መክብብ 9:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 እጅህ የሚያገኘውን ሥራ ሁሉ በሙሉ ኃይልህ አከናውን፤ አንተ በምትሄድበት በመቃብር* ሥራም ሆነ ዕቅድ፣ እውቀትም ሆነ ጥበብ የለምና።+ ሕዝቅኤል 18:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 እነሆ፣ ነፍስ* ሁሉ የእኔ ነው። የአባት ነፍስ የእኔ እንደሆነች ሁሉ የልጅም ነፍስ የእኔ ናት። ኃጢአት የምትሠራ ነፍስ እሷ ትሞታለች።* ሮም 5:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 ስለሆነም በአንድ ሰው አማካኝነት ኃጢአት ወደ ዓለም ገባ፤+ በኃጢአትም ምክንያት ሞት መጣ፤ ሁሉም ኃጢአት ስለሠሩም ሞት ለሰው ሁሉ ተዳረሰ።+ 1 ቆሮንቶስ 15:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 ሁሉም በአዳም እንደሚሞቱ+ ሁሉም በክርስቶስ ሕያው ይሆናሉና።+