ዘፍጥረት 23:3, 4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ከዚያም አብርሃም ከሚስቱ አስከሬን አጠገብ ተነሳ፤ የሄትንም+ ወንዶች ልጆች እንዲህ አላቸው፦ 4 “እኔ በመካከላችሁ የምኖር የባዕድ አገር ሰውና ሰፋሪ ነኝ።+ አስከሬኔን ወስጄ እንድቀብር በመካከላችሁ የመቃብር ቦታ የሚሆን መሬት ስጡኝ።” ዘፍጥረት 28:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 28 በመሆኑም ይስሐቅ ያዕቆብን ጠርቶ ባረከውና እንዲህ ሲል አዘዘው፦ “ከከነአን ሴቶች ልጆች ሚስት እንዳታገባ።+ ዘፍጥረት 28:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 አምላክ ለአብርሃም የሰጠውን፣+ አንተም እንደ ባዕድ አገር ሰው ሆነህ የምትኖርበትን ምድር እንድትወርስ የአብርሃምን በረከት+ ለአንተና ከአንተ ጋር ላለው ዘርህ ይሰጣል።” ዕብራውያን 11:8, 9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 አብርሃም+ በተጠራ ጊዜ ወደፊት ርስት አድርጎ ወደሚቀበለው ስፍራ በመሄድ በእምነት ታዘዘ፤ ወዴት እንደሚሄድ ባያውቅም ይኖርበት የነበረውን ስፍራ ለቆ ወጣ።+ 9 በባዕድ አገር እንደሚኖር እንግዳ በተስፋይቱ ምድር በእምነት ኖረ፤+ ደግሞም አብረውት የዚሁ ተስፋ ቃል ወራሾች ከሆኑት ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር+ በድንኳን ኖረ።+
3 ከዚያም አብርሃም ከሚስቱ አስከሬን አጠገብ ተነሳ፤ የሄትንም+ ወንዶች ልጆች እንዲህ አላቸው፦ 4 “እኔ በመካከላችሁ የምኖር የባዕድ አገር ሰውና ሰፋሪ ነኝ።+ አስከሬኔን ወስጄ እንድቀብር በመካከላችሁ የመቃብር ቦታ የሚሆን መሬት ስጡኝ።”
4 አምላክ ለአብርሃም የሰጠውን፣+ አንተም እንደ ባዕድ አገር ሰው ሆነህ የምትኖርበትን ምድር እንድትወርስ የአብርሃምን በረከት+ ለአንተና ከአንተ ጋር ላለው ዘርህ ይሰጣል።”
8 አብርሃም+ በተጠራ ጊዜ ወደፊት ርስት አድርጎ ወደሚቀበለው ስፍራ በመሄድ በእምነት ታዘዘ፤ ወዴት እንደሚሄድ ባያውቅም ይኖርበት የነበረውን ስፍራ ለቆ ወጣ።+ 9 በባዕድ አገር እንደሚኖር እንግዳ በተስፋይቱ ምድር በእምነት ኖረ፤+ ደግሞም አብረውት የዚሁ ተስፋ ቃል ወራሾች ከሆኑት ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር+ በድንኳን ኖረ።+