-
ዘፍጥረት 24:34አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
34 እሱም እንዲህ አለ፦ “እኔ የአብርሃም አገልጋይ ነኝ።+
-
-
ዘፍጥረት 24:37አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
37 በመሆኑም ጌታዬ እንዲህ በማለት አስማለኝ፦ ‘በአገራቸው ከምኖረው ከከነአናውያን ሴቶች ልጆች መካከል ለልጄ ሚስት እንዳታመጣለት።+
-
-
1 ነገሥት 11:1-3አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
11 ይሁንና ንጉሥ ሰለሞን ከፈርዖን ልጅ+ ሌላ ብዙ የባዕድ አገር ሴቶችን+ ማለትም ሞዓባውያን፣+ አሞናውያን፣+ ኤዶማውያን፣ ሲዶናውያንና+ ሂታውያን+ ሴቶችን አፈቀረ። 2 እነሱም ይሖዋ ለእስራኤላውያን “ከእነሱ ጋር አትቀላቀሉ፤* እነሱም ከእናንተ ጋር አይቀላቀሉ፤ አለዚያ ያለምንም ጥርጥር ልባችሁ አማልክታቸውን ወደ መከተል እንዲያዘነብል ያደርጉታል”+ ብሎ ከነገራቸው ብሔራት ወገን ነበሩ። ሆኖም ሰለሞን ከእነሱ ጋር ተጣበቀ፤ ደግሞም አፈቀራቸው። 3 እሱም ልዕልቶች የሆኑ 700 ሚስቶች እንዲሁም 300 ቁባቶች ነበሩት፤ ሚስቶቹም ቀስ በቀስ ልቡ ወደ ሌላ እንዲያዘነብል አደረጉት።*
-