ዘፀአት 3:19, 20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 ይሁንና የግብፁ ንጉሥ ኃያል የሆነ ክንድ ካላስገደደው በስተቀር እንድትሄዱ እንደማይፈቅድላችሁ እኔ ራሴ በሚገባ አውቃለሁ።+ 20 በመሆኑም እጄን እዘረጋለሁ፤ ግብፅንም በመካከሏ በምፈጽማቸው ድንቅ ነገሮች ሁሉ እመታለሁ፤ ከዚያ በኋላ ይለቃችኋል።+ መዝሙር 105:26, 27 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 26 አገልጋዩን ሙሴን፣+የመረጠውንም አሮንን ላከ።+ 27 እነሱም ምልክቶቹን በመካከላቸው፣ተአምራቱን በካም ምድር አደረጉ።+ የሐዋርያት ሥራ 7:36 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 36 ይህ ሰው በግብፅ፣ በቀይ ባሕርና+ በምድረ በዳ ለ40 ዓመት+ ድንቅ ነገሮችንና ተአምራዊ ምልክቶችን በመፈጸም+ ከግብፅ እየመራ አወጣቸው።+
19 ይሁንና የግብፁ ንጉሥ ኃያል የሆነ ክንድ ካላስገደደው በስተቀር እንድትሄዱ እንደማይፈቅድላችሁ እኔ ራሴ በሚገባ አውቃለሁ።+ 20 በመሆኑም እጄን እዘረጋለሁ፤ ግብፅንም በመካከሏ በምፈጽማቸው ድንቅ ነገሮች ሁሉ እመታለሁ፤ ከዚያ በኋላ ይለቃችኋል።+