ዘፀአት 14:21, 22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 ሙሴም እጁን በባሕሩ ላይ ሰነዘረ፤+ ይሖዋም ሌሊቱን ሙሉ ኃይለኛ የምሥራቅ ነፋስ በማምጣት ባሕሩ ወደ ኋላ እንዲመለስ አደረገ፤ የባሕሩንም ወለል ወደ ደረቅ መሬት ለወጠው፤+ ውኃውም ተከፈለ።+ 22 በመሆኑም እስራኤላውያን ውኃው በቀኛቸውና በግራቸው እንደ ግድግዳ ቆሞ+ በባሕሩ መሃል በደረቅ መሬት ተሻገሩ።+ ዘፀአት 15:4, 5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 የፈርዖንን ሠረገሎችና ሠራዊቱን ባሕር ውስጥ ወረወራቸው፣+ ምርጥ የሆኑ ተዋጊዎቹም ቀይ ባሕር ውስጥ ሰመጡ።+ 5 ማዕበሉም ከደናቸው፤ እነሱም እንደ ድንጋይ ወደ ጥልቁ ሰመጡ።+
21 ሙሴም እጁን በባሕሩ ላይ ሰነዘረ፤+ ይሖዋም ሌሊቱን ሙሉ ኃይለኛ የምሥራቅ ነፋስ በማምጣት ባሕሩ ወደ ኋላ እንዲመለስ አደረገ፤ የባሕሩንም ወለል ወደ ደረቅ መሬት ለወጠው፤+ ውኃውም ተከፈለ።+ 22 በመሆኑም እስራኤላውያን ውኃው በቀኛቸውና በግራቸው እንደ ግድግዳ ቆሞ+ በባሕሩ መሃል በደረቅ መሬት ተሻገሩ።+
4 የፈርዖንን ሠረገሎችና ሠራዊቱን ባሕር ውስጥ ወረወራቸው፣+ ምርጥ የሆኑ ተዋጊዎቹም ቀይ ባሕር ውስጥ ሰመጡ።+ 5 ማዕበሉም ከደናቸው፤ እነሱም እንደ ድንጋይ ወደ ጥልቁ ሰመጡ።+