የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘፍጥረት 12:1, 2
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 12 ይሖዋም አብራምን እንዲህ አለው፦ “ከአገርህ፣ ከዘመዶችህና ከአባትህ ቤት ወጥተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ሂድ።+ 2 አንተን ታላቅ ብሔር አደርግሃለሁ፤ እንዲሁም እባርክሃለሁ፤ ስምህንም ታላቅ አደርገዋለሁ፤ አንተም በረከት ትሆናለህ።+

  • ዘፍጥረት 15:1
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 15 ከዚህ በኋላ የይሖዋ ቃል በራእይ ወደ አብራም መጥቶ “አብራም አትፍራ።+ እኔ ጋሻ እሆንሃለሁ።+ የምታገኘውም ሽልማት እጅግ ታላቅ ይሆናል”+ አለው።

  • ዘፍጥረት 15:5
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 5 ወደ ውጭም ካወጣው በኋላ “እባክህ ቀና ብለህ ወደ ሰማይ ተመልከት፤ እስቲ መቁጠር ከቻልክ ከዋክብቱን ቁጠራቸው” አለው። ከዚያም “የአንተም ዘር እንዲሁ ይሆናል”+ አለው።

  • ዘፍጥረት 46:2, 3
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 2 ከዚያም አምላክ ለእስራኤል ሌሊት በራእይ ተገልጦለት “ያዕቆብ፣ ያዕቆብ!” ሲል ጠራው፤ እሱም “አቤት!” አለ። 3 አምላክም እንዲህ አለው፦ “እኔ የአባትህ አምላክ የሆንኩት እውነተኛው አምላክ ነኝ።+ ወደ ግብፅ ለመውረድ አትፍራ፤ ምክንያቱም በዚያ ታላቅ ብሔር አደርግሃለሁ።+

  • ዘፀአት 1:7
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 7 እስራኤላውያንም* ተዋለዱ፤ በጣም ብዙ ሆኑ፤ ቁጥራቸውም በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረና ኃያል እየሆኑ ሄዱ፤ ከዚህም የተነሳ ምድሪቱን ሞሏት።+

  • ዘኁልቁ 2:32
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 32 በአባቶቻቸው ቤት መሠረት የተመዘገቡት እስራኤላውያን እነዚህ ነበሩ፤ ወደ ሠራዊቱ ለመቀላቀል በሰፈሩ ውስጥ የተመዘገቡት በአጠቃላይ 603,550 ነበሩ።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ