ዘኁልቁ 9:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 ከእሱም ላይ እስከ ጠዋት ድረስ ምንም ማስተረፍ+ ወይም ከአጥንቱ ውስጥ አንዱንም መስበር+ የለባቸውም። ፋሲካን በተመለከተ የወጣውን ደንብ ሁሉ ተከትለው ያዘጋጁት። መዝሙር 34:19, 20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 የጻድቅ ሰው መከራ* ብዙ ነው፤+ይሖዋ ግን ከመከራው ሁሉ ይታደገዋል።+ ש [ሺን] 20 አጥንቶቹን ሁሉ ይጠብቃል፤አንዳቸውም ቢሆኑ አልተሰበሩም።+ ዮሐንስ 19:33 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 33 ወደ ኢየሱስ በመጡ ጊዜ ግን ቀደም ብሎ መሞቱን ስላዩ እግሮቹን አልሰበሩም። ዮሐንስ 19:36 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 36 ይህም የሆነው “ከእሱ አንድ አጥንት እንኳ አይሰበርም”+ የሚለው የቅዱስ መጽሐፉ ቃል እንዲፈጸም ነው።
12 ከእሱም ላይ እስከ ጠዋት ድረስ ምንም ማስተረፍ+ ወይም ከአጥንቱ ውስጥ አንዱንም መስበር+ የለባቸውም። ፋሲካን በተመለከተ የወጣውን ደንብ ሁሉ ተከትለው ያዘጋጁት።