ዘኁልቁ 3:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ምክንያቱም በኩር ሁሉ የእኔ ነው።+ በግብፅ ምድር ያለውን በኩር ሁሉ በመታሁበት ቀን+ በእስራኤላውያን መካከል ያለውን የሰውም ሆነ የእንስሳ በኩር ለራሴ ቀድሻለሁ።+ እነሱ የእኔ ይሆናሉ። እኔ ይሖዋ ነኝ።” ዘኁልቁ 18:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 “ከሰውም ሆነ ከእንስሳ ለይሖዋ የሚያቀርቡት የእያንዳንዱ ሕይወት ያለው ነገር* በኩር ሁሉ+ የአንተ መሆን ይኖርበታል። ሆኖም ከሰው በኩር የሆነውን ሁሉ መዋጀት ይኖርብሃል፤+ እንዲሁም ርኩስ ከሆነ እንስሳ በኩር የሆነውን ሁሉ መዋጀት ይገባሃል።+ ዘዳግም 15:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 “ከከብትህና ከመንጋህ መካከል በኩር የሆነውን ወንድ ሁሉ ለአምላክህ ለይሖዋ ቀድሰው።+ በከብትህ* በኩር ምንም ሥራ አትሥራበት፤ የመንጋህንም በኩር አትሸልት። ሉቃስ 2:22, 23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 በተጨማሪም በሙሴ ሕግ መሠረት+ የሚነጹበት ጊዜ ሲደርስ ሕፃኑን በይሖዋ* ፊት ለማቅረብ ወደ ኢየሩሳሌም ይዘውት መጡ፤ 23 ይህን ያደረጉት “በኩር የሆነ ወንድ ሁሉ* ለይሖዋ* የተቀደሰ መሆን አለበት”+ ተብሎ በይሖዋ* ሕግ ላይ በተጻፈው መሠረት ነው።
13 ምክንያቱም በኩር ሁሉ የእኔ ነው።+ በግብፅ ምድር ያለውን በኩር ሁሉ በመታሁበት ቀን+ በእስራኤላውያን መካከል ያለውን የሰውም ሆነ የእንስሳ በኩር ለራሴ ቀድሻለሁ።+ እነሱ የእኔ ይሆናሉ። እኔ ይሖዋ ነኝ።”
15 “ከሰውም ሆነ ከእንስሳ ለይሖዋ የሚያቀርቡት የእያንዳንዱ ሕይወት ያለው ነገር* በኩር ሁሉ+ የአንተ መሆን ይኖርበታል። ሆኖም ከሰው በኩር የሆነውን ሁሉ መዋጀት ይኖርብሃል፤+ እንዲሁም ርኩስ ከሆነ እንስሳ በኩር የሆነውን ሁሉ መዋጀት ይገባሃል።+
19 “ከከብትህና ከመንጋህ መካከል በኩር የሆነውን ወንድ ሁሉ ለአምላክህ ለይሖዋ ቀድሰው።+ በከብትህ* በኩር ምንም ሥራ አትሥራበት፤ የመንጋህንም በኩር አትሸልት።
22 በተጨማሪም በሙሴ ሕግ መሠረት+ የሚነጹበት ጊዜ ሲደርስ ሕፃኑን በይሖዋ* ፊት ለማቅረብ ወደ ኢየሩሳሌም ይዘውት መጡ፤ 23 ይህን ያደረጉት “በኩር የሆነ ወንድ ሁሉ* ለይሖዋ* የተቀደሰ መሆን አለበት”+ ተብሎ በይሖዋ* ሕግ ላይ በተጻፈው መሠረት ነው።