ዘፀአት 13:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 “ከእስራኤል ሕዝብ መካከል በኩር የሆነውን ወንድ ሁሉ ለእኔ ቀድስልኝ።* ከሰውም ሆነ ከእንስሳ መካከል በኩር የሆነው ወንድ ሁሉ* የእኔ ነው።”+ ዘፀአት 13:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 በኩር የሆነውን ወንድ ሁሉ* እንዲሁም የአንተ ከሆነው እንስሳ መካከል በኩር የሆነውን ወንድ ሁሉ ለይሖዋ መስጠት አለብህ። ወንዶቹ ሁሉ የይሖዋ ናቸው።+ ዘፀአት 22:29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 “ከተትረፈረፈው ምርትህና ሞልቶ ከሚፈሰው መጭመቂያህ* መባ ለማቅረብ አትሳሳ።+ የወንዶች ልጆችህን በኩር ለእኔ መስጠት አለብህ።+ ዘኁልቁ 3:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ምክንያቱም በኩር ሁሉ የእኔ ነው።+ በግብፅ ምድር ያለውን በኩር ሁሉ በመታሁበት ቀን+ በእስራኤላውያን መካከል ያለውን የሰውም ሆነ የእንስሳ በኩር ለራሴ ቀድሻለሁ።+ እነሱ የእኔ ይሆናሉ። እኔ ይሖዋ ነኝ።” ዘኁልቁ 8:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 ምክንያቱም ሰውም ሆነ እንስሳ ከእስራኤላውያን መካከል በኩር የሆነ ሁሉ የእኔ ነው።+ በግብፅ ምድር ያለውን በኩር ሁሉ በመታሁበት ቀን እነሱን ለራሴ ቀድሻቸዋለሁ።+
13 ምክንያቱም በኩር ሁሉ የእኔ ነው።+ በግብፅ ምድር ያለውን በኩር ሁሉ በመታሁበት ቀን+ በእስራኤላውያን መካከል ያለውን የሰውም ሆነ የእንስሳ በኩር ለራሴ ቀድሻለሁ።+ እነሱ የእኔ ይሆናሉ። እኔ ይሖዋ ነኝ።”
17 ምክንያቱም ሰውም ሆነ እንስሳ ከእስራኤላውያን መካከል በኩር የሆነ ሁሉ የእኔ ነው።+ በግብፅ ምድር ያለውን በኩር ሁሉ በመታሁበት ቀን እነሱን ለራሴ ቀድሻቸዋለሁ።+