ዘዳግም 31:23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 እሱም* የነዌን ልጅ ኢያሱን ሾመው፤+ እንዲህም አለው፦ “ደፋርና ብርቱ ሁን፤+ ምክንያቱም እስራኤላውያንን ወደማልኩላቸው ምድር የምታስገባቸው አንተ ነህ፤+ እኔም ምንጊዜም ከአንተ ጋር እሆናለሁ።” ኢያሱ 1:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 በሕይወት ዘመንህ ሁሉ ማንም አይቋቋምህም።+ ከሙሴ ጋር እንደነበርኩ ሁሉ ከአንተም ጋር እሆናለሁ።+ አልጥልህም ወይም አልተውህም።+ ኢሳይያስ 41:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ።+ እኔ አምላክህ ነኝና አትጨነቅ።+ አበረታሃለሁ፤ አዎ እረዳሃለሁ፤+በጽድቅ ቀኝ እጄ አጥብቄ እይዝሃለሁ።’ ሮም 8:31 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 31 እንግዲህ ስለ እነዚህ ነገሮች ምን እንበል? አምላክ ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ሊቃወመን ይችላል?+ ፊልጵስዩስ 4:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ኃይልን በሚሰጠኝ በእሱ አማካኝነት ለሁሉም ነገር የሚሆን ብርታት አለኝ።+
23 እሱም* የነዌን ልጅ ኢያሱን ሾመው፤+ እንዲህም አለው፦ “ደፋርና ብርቱ ሁን፤+ ምክንያቱም እስራኤላውያንን ወደማልኩላቸው ምድር የምታስገባቸው አንተ ነህ፤+ እኔም ምንጊዜም ከአንተ ጋር እሆናለሁ።”