ዘፀአት 15:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ይሖዋ ኃያል ተዋጊ ነው።+ ስሙ ይሖዋ ነው።+ መዝሙር 96:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ለስሙ የሚገባውን ክብር ለይሖዋ ስጡ፤+ስጦታ ይዛችሁ ወደ ቅጥር ግቢዎቹ ግቡ። መዝሙር 135:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ይሖዋ ሆይ፣ ስምህ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል። ይሖዋ ሆይ፣ ዝናህ* ከትውልድ እስከ ትውልድ ይዘልቃል።+ ሆሴዕ 12:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 እሱ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ ነው።+የመታሰቢያ ስሙ* ይሖዋ ነው።+ ዮሐንስ 17:26 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 26 እኔን የወደድክበት ፍቅር እነሱም እንዲኖራቸው እንዲሁም እኔ ከእነሱ ጋር አንድነት እንዲኖረኝ+ ስምህን አሳውቄአቸዋለሁ፤ ደግሞም አሳውቃለሁ።”+ ሮም 10:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 “የይሖዋን* ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናልና።”+