-
ዘፀአት 35:4-9አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
4 ከዚያም ሙሴ ለእስራኤል ማኅበረሰብ ሁሉ እንዲህ አለ፦ “ይሖዋ እንዲህ ሲል አዟል፦ 5 ‘ካላችሁ ነገር ለይሖዋ መዋጮ አምጡ።+ ልቡ ያነሳሳው+ ማንኛውም ሰው የሚከተሉትን ነገሮች ለይሖዋ መዋጮ አድርጎ ያምጣ፦ ወርቅ፣ ብር፣ መዳብ፣ 6 ሰማያዊ ክር፣ ሐምራዊ ሱፍ፣ ደማቅ ቀይ ማግ፣ ጥሩ በፍታ፣ የፍየል ፀጉር፣+ 7 ቀይ ቀለም የተነከረ የአውራ በግ ቆዳ፣ የአቆስጣ ቆዳ፣ የግራር እንጨት፣ 8 ለመብራት የሚሆን ዘይት፣ ለቅብዓት ዘይትና ጥሩ መዓዛ ላለው ዕጣን የሚሆን የበለሳን ዘይት፣+ 9 በኤፉዱና በደረት ኪሱ+ ላይ የሚቀመጡ የኦኒክስ ድንጋዮችና+ ሌሎች ድንጋዮች።
-
-
1 ዜና መዋዕል 29:9አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
9 ሕዝቡ በፈቃደኝነት መባ በመስጠታቸው እጅግ ተደሰቱ፤ በፈቃደኝነት ተነሳስተው ለይሖዋ መባ የሰጡት በሙሉ ልባቸው ነበርና፤+ ንጉሥ ዳዊትም እጅግ ደስ አለው።
-