ዘፀአት 29:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 “አሮንንና ወንዶች ልጆቹን ወደ መገናኛ ድንኳኑ መግቢያ+ ታቀርባቸዋለህ፤ በውኃም ታጥባቸዋለህ።+ ዘፀአት 29:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 የቅብዓት ዘይቱንም+ ወስደህ በራሱ ላይ በማፍሰስ ትቀባዋለህ።+ ዘፀአት 30:30 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 30 አንተም አሮንንና ወንዶች ልጆቹን ትቀባቸዋለህ፤+ ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉኝም+ ትቀድሳቸዋለህ። የሐዋርያት ሥራ 10:38 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 38 የተወራውም ስለ ናዝሬቱ ኢየሱስ ነው። አምላክ በመንፈስ ቅዱስ ቀባው፤+ ደግሞም ኃይል ሰጠው፤ ኢየሱስም አምላክ ከእሱ ጋር ስለነበር መልካም ነገር እያደረገና+ በዲያብሎስ ቁጥጥር ሥር የወደቁትን እየፈወሰ+ በዚያ አገር ሁሉ ተዘዋወረ። 2 ቆሮንቶስ 1:21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 ይሁንና እኛም ሆን እናንተ የክርስቶስ ለመሆናችን ዋስትና የሰጠንና የቀባን አምላክ ነው።+
38 የተወራውም ስለ ናዝሬቱ ኢየሱስ ነው። አምላክ በመንፈስ ቅዱስ ቀባው፤+ ደግሞም ኃይል ሰጠው፤ ኢየሱስም አምላክ ከእሱ ጋር ስለነበር መልካም ነገር እያደረገና+ በዲያብሎስ ቁጥጥር ሥር የወደቁትን እየፈወሰ+ በዚያ አገር ሁሉ ተዘዋወረ።