-
ዘፀአት 29:38-42አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
38 “በመሠዊያውም ላይ የምታቀርበው እነዚህን ይሆናል፦ አንድ ዓመት የሆናቸው ሁለት የበግ ጠቦቶችን በየቀኑ ሳታቋርጥ ታቀርባለህ።+ 39 አንደኛውን የበግ ጠቦት ጠዋት ላይ ታቀርበዋለህ፤ ሌላኛውን የበግ ጠቦት ደግሞ አመሻሹ ላይ* ታቀርበዋለህ።+ 40 ተጨቅጭቆ በተጠለለ አንድ አራተኛ ሂን* ዘይት የተለወሰ የኢፍ መስፈሪያ* አንድ አሥረኛ የላመ ዱቄትና ለመጠጥ መባ የሚሆን አንድ አራተኛ ሂን የወይን ጠጅ ከመጀመሪያው የበግ ጠቦት ጋር ይቅረብ። 41 ሁለተኛውንም የበግ ጠቦት ልክ ማለዳ ላይ ከምታቀርባቸው ጋር ተመሳሳይ ከሆኑ የእህልና የመጠጥ መባዎች ጋር አመሻሹ ላይ* ታቀርበዋለህ። ይህን ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ ይኸውም ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ አድርገህ ታቀርበዋለህ። 42 ይህም እኔ እናንተን ለማነጋገር ራሴን በምገልጥበት በመገናኛ ድንኳኑ+ መግቢያ ላይ በመጪዎቹ ትውልዶቻችሁ ሁሉ በይሖዋ ፊት ዘወትር የሚቀርብ የሚቃጠል መባ ይሆናል።
-
-
ዘኁልቁ 28:3አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
3 “እንዲህም በላቸው፦ ‘ለይሖዋ የምታቀርቡት በእሳት የሚቃጠል መባ ይህ ነው፦ በየቀኑ፣ አንድ ዓመት የሆናቸው እንከን የሌለባቸው ሁለት ተባዕት የበግ ጠቦቶችን የሚቃጠል መባ አድርጋችሁ ዘወትር አቅርቡ።+
-