ዘሌዋውያን 20:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 “‘አንድ ሰው* ከመናፍስት ጠሪዎችና+ ከጠንቋዮች+ ጋር መንፈሳዊ ምንዝር ለመፈጸም ወደ እነሱ ቢሄድ እኔ በዚያ ሰው* ላይ በእርግጥ እነሳበታለሁ፤ ከሕዝቡም መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ።+ ዘዳግም 18:10-12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን በእሳት የሚያሳልፍ፣+ ሟርተኛ፣+ አስማተኛ፣+ ሞራ ገላጭ፣+ ምትሃተኛ፣+ 11 ድግምተኛ፣ መናፍስት ጠሪ፣+ ጠንቋይ+ ወይም ሙታን አነጋጋሪ+ በመካከልህ አይገኝ። 12 ምክንያቱም እነዚህን ነገሮች የሚያደርግ ሰው ሁሉ በይሖዋ ፊት አስጸያፊ ነው፤ አምላክህ ይሖዋም እነሱን ከፊትህ የሚያባርራቸው በእነዚህ አስጸያፊ ነገሮች የተነሳ ነው። 1 ዜና መዋዕል 10:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ስለዚህ ሳኦል ለይሖዋ ታማኝ ሳይሆን በመቅረቱ ሞተ፤ ምክንያቱም የይሖዋን ቃል አልታዘዘም፤+ ደግሞም መናፍስት ጠሪን አማከረ፤+ ኢሳይያስ 8:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 እነሱም “የሚያነበንቡትንና የሚያንሾካሹኩትን መናፍስት ጠሪዎች ወይም ጠንቋዮች ጠይቁ” ቢሏችሁ፣ አንድ ሕዝብ መጠየቅ ያለበት የራሱን አምላክ አይደለም? ስለ ሕያዋንስ ሙታንን መጠየቁ ተገቢ ነው?+
6 “‘አንድ ሰው* ከመናፍስት ጠሪዎችና+ ከጠንቋዮች+ ጋር መንፈሳዊ ምንዝር ለመፈጸም ወደ እነሱ ቢሄድ እኔ በዚያ ሰው* ላይ በእርግጥ እነሳበታለሁ፤ ከሕዝቡም መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ።+
10 ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን በእሳት የሚያሳልፍ፣+ ሟርተኛ፣+ አስማተኛ፣+ ሞራ ገላጭ፣+ ምትሃተኛ፣+ 11 ድግምተኛ፣ መናፍስት ጠሪ፣+ ጠንቋይ+ ወይም ሙታን አነጋጋሪ+ በመካከልህ አይገኝ። 12 ምክንያቱም እነዚህን ነገሮች የሚያደርግ ሰው ሁሉ በይሖዋ ፊት አስጸያፊ ነው፤ አምላክህ ይሖዋም እነሱን ከፊትህ የሚያባርራቸው በእነዚህ አስጸያፊ ነገሮች የተነሳ ነው።
19 እነሱም “የሚያነበንቡትንና የሚያንሾካሹኩትን መናፍስት ጠሪዎች ወይም ጠንቋዮች ጠይቁ” ቢሏችሁ፣ አንድ ሕዝብ መጠየቅ ያለበት የራሱን አምላክ አይደለም? ስለ ሕያዋንስ ሙታንን መጠየቁ ተገቢ ነው?+