ዘፀአት 19:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 አሁንም ቃሌን በጥብቅ ብትታዘዙና ቃል ኪዳኔን ብትጠብቁ መላው ምድር የእኔ ስለሆነ+ እናንተ ከሌሎች ሕዝቦች ሁሉ የተመረጣችሁ ልዩ ንብረቶቼ* ትሆናላችሁ።+ ዘሌዋውያን 20:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ደንቦቼን ጠብቁ፤ እንዲሁም ፈጽሟቸው።+ የምቀድሳችሁ እኔ ይሖዋ ነኝ።+ ዘሌዋውያን 21:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 የአምላክህን ምግብ የሚያቀርበው እሱ ስለሆነ ቀድሰው።+ እናንተን የምቀድሳችሁ እኔ ይሖዋ ቅዱስ ስለሆንኩ እሱም በአንተ ፊት ቅዱስ ሆኖ መገኘት አለበት።+