ዘፀአት 20:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 “የአምላክህን የይሖዋን ስም በከንቱ አታንሳ፤+ ምክንያቱም ይሖዋ ስሙን በከንቱ የሚያነሳውን ሳይቀጣ አይተወውም።+ ዘፀአት 22:28 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 28 “አምላክን አትራገም፤+ በሕዝብህ መካከል ያለውን አለቃም* አትራገም።+ ዘሌዋውያን 19:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 በስሜ በሐሰት አትማሉ፤+ በዚህም የአምላካችሁን ስም አታርክሱ። እኔ ይሖዋ ነኝ።