የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘሌዋውያን 19
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘሌዋውያን የመጽሐፉ ይዘት

      • ቅድስናን አስመልክቶ የተሰጡ ሕጎች (1-37)

        • አዝመራ የሚሰበሰብበት ትክክለኛ አሠራር (9, 10)

        • መስማት ለተሳናቸውና ለዓይነ ስውሮች አሳቢነት ማሳየት (14)

        • ስም ማጥፋት (16)

        • ቂም አትያዝ (18)

        • ጥንቆላና መናፍስታዊ ድርጊት የተከለከለ ነው (26, 31)

        • ሰውነትን መነቀስ የተከለከለ ነው (28)

        • አረጋውያንን አክብር (32)

        • ለባዕድ አገር ሰው አሳቢነት ማሳየት (33, 34)

ዘሌዋውያን 19:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 11:44፤ ኢሳ 6:3፤ 1ጴጥ 1:15, 16፤ ራእይ 4:8

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    12/2021፣ ገጽ 3-4

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/1/2009፣ ገጽ 9

    8/1/1996፣ ገጽ 10-11

ዘሌዋውያን 19:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ይፍራ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 20:12፤ ኤፌ 6:2፤ ዕብ 12:9
  • +ዘፀ 20:8, 11፤ 31:13፤ ሉቃስ 6:5

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    12/2021፣ ገጽ 4-5, 8

ዘሌዋውያን 19:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 26:1፤ መዝ 96:5፤ ዕን 2:18፤ 1ቆሮ 10:14
  • +ዘፀ 20:4, 23፤ ዘዳ 27:15

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    12/2021፣ ገጽ 5-6

ዘሌዋውያን 19:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 3:1
  • +ዘሌ 7:11, 12

ዘሌዋውያን 19:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 7:17, 18

ዘሌዋውያን 19:8

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍስ።”

ዘሌዋውያን 19:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 23:22፤ ዘዳ 24:19

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    6/15/2006፣ ገጽ 22-23

    12/1/2003፣ ገጽ 17

ዘሌዋውያን 19:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ለጎስቋላውና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 15:7

ዘሌዋውያን 19:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 20:15፤ ኤፌ 4:28
  • +ዘሌ 6:2፤ ምሳሌ 12:22፤ ኤፌ 4:25

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    12/2021፣ ገጽ 10

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    12/2016፣ ገጽ 11-12

ዘሌዋውያን 19:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 20:7፤ ማቴ 5:33, 37፤ ያዕ 5:12

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    12/2021፣ ገጽ 10

ዘሌዋውያን 19:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ምሳሌ 22:16፤ ማር 10:19
  • +ምሳሌ 22:22
  • +ዘዳ 24:15፤ ኤር 22:13፤ ያዕ 5:4

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    12/2021፣ ገጽ 10

ዘሌዋውያን 19:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 27:18
  • +ዘሌ 25:17፤ ነህ 5:15፤ ምሳሌ 1:7፤ 8:13፤ 1ጴጥ 2:17

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    12/2021፣ ገጽ 8-9

ዘሌዋውያን 19:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 23:3፤ ዘዳ 1:16, 17፤ 16:19፤ 2ዜና 19:6፤ ሮም 2:11፤ ያዕ 2:9

ዘሌዋውያን 19:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ደም።”

  • *

    “የባልንጀራህ ሕይወት ለአደጋ ሲጋለጥ ዝም ብለህ አትመልከት” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 15:1, 3
  • +ዘፀ 20:16፤ 1ነገ 21:13

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    12/2021፣ ገጽ 14

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ 7/2021፣ ገጽ 6

ዘሌዋውያን 19:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ምሳሌ 10:18፤ 1ዮሐ 2:9፤ 3:15
  • +መዝ 141:5፤ ምሳሌ 9:8፤ ማቴ 18:15

ዘሌዋውያን 19:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ምሳሌ 20:22፤ ሮም 12:19
  • +ማቴ 5:43, 44፤ 22:39፤ ሮም 13:9፤ ገላ 5:14፤ ያዕ 2:8

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው፣ ርዕስ 134, 195

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    12/2021፣ ገጽ 10-12

    መጠበቂያ ግንብ፣

    4/15/2011፣ ገጽ 22

    12/1/2006፣ ገጽ 26-27

    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ጥራዝ 6፣ ገጽ 1

ዘሌዋውያን 19:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 22:9
  • +ዘዳ 22:11

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    12/2021፣ ገጽ 6

ዘሌዋውያን 19:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 6:6, 7

ዘሌዋውያን 19:23

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “እንደ ፍሬው ሸለፈት።”

  • *

    ቃል በቃል “ለእናንተ እንዳልተገረዘ ይሆናል።”

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    12/2021፣ ገጽ 6-7

ዘሌዋውያን 19:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 26:1, 2፤ ምሳሌ 3:9

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    12/2021፣ ገጽ 6-7

ዘሌዋውያን 19:25

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    12/2021፣ ገጽ 6-7

ዘሌዋውያን 19:26

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 3:17፤ 17:13፤ ዘዳ 12:23፤ ሥራ 15:20, 29
  • +ዘፀ 8:7፤ ዘዳ 18:10-12፤ ገላ 5:19, 20፤ ራእይ 21:8

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ንቁ!፣

    7/8/1994፣ ገጽ 29

ዘሌዋውያን 19:27

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “አትከርክሙ፤ አትቁረጡ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 21:1, 5

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    5/15/2004፣ ገጽ 24

    ንቁ!፣

    2/8/2000፣ ገጽ 14-16

ዘሌዋውያን 19:28

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍስ።” እዚህ ቦታ ላይ የገባው ነፈሽ የሚለው የዕብራይስጥ ቃል የሞተን ሰው የሚያመለክት ነው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 14:1

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው፣ ርዕስ 50

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ 1/2021፣ ገጽ 3

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/15/2003፣ ገጽ 27

    ንቁ!፣

    8/8/2000፣ ገጽ 20-21

ዘሌዋውያን 19:29

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕብ 13:4፤ 1ጴጥ 4:3
  • +ዘዳ 23:17

ዘሌዋውያን 19:30

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “አድናቆት።” ቃል በቃል “ፍርሃት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 20:10፤ 31:13

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ 1/2021፣ ገጽ 6

ዘሌዋውያን 19:31

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 20:6፤ ዘዳ 18:10-12፤ 1ዜና 10:13፤ ኢሳ 8:19
  • +ዘሌ 20:27፤ ሥራ 16:16

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 24

ዘሌዋውያን 19:32

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ምሳሌ 16:31፤ 20:29
  • +ኢዮብ 32:6፤ ምሳሌ 23:22፤ 1ጢሞ 5:1
  • +ኢዮብ 28:28፤ ምሳሌ 1:7፤ 8:13፤ 1ጴጥ 2:17

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/15/2008፣ ገጽ 21

    6/15/2000፣ ገጽ 21

    8/1/1999፣ ገጽ 20

    8/1/1994፣ ገጽ 27

    3/15/1993፣ ገጽ 27

    ንቁ!፣

    11/8/2004፣ ገጽ 22-23

    የቤተሰብ ደስታ፣ ገጽ 149

ዘሌዋውያን 19:33

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 23:9

ዘሌዋውያን 19:34

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 12:49
  • +ዘፀ 22:21

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    12/2021፣ ገጽ 12-13

ዘሌዋውያን 19:35

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 25:13, 15፤ ምሳሌ 20:10

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    12/2021፣ ገጽ 10

ዘሌዋውያን 19:36

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ትክክለኛ ኢፍና።” ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።

  • *

    ቃል በቃል “ትክክለኛ ሂን።” ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ምሳሌ 11:1

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    12/2021፣ ገጽ 10

ዘሌዋውያን 19:37

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 18:5፤ ዘዳ 4:6

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘሌ. 19:2ዘሌ 11:44፤ ኢሳ 6:3፤ 1ጴጥ 1:15, 16፤ ራእይ 4:8
ዘሌ. 19:3ዘፀ 20:12፤ ኤፌ 6:2፤ ዕብ 12:9
ዘሌ. 19:3ዘፀ 20:8, 11፤ 31:13፤ ሉቃስ 6:5
ዘሌ. 19:4ዘሌ 26:1፤ መዝ 96:5፤ ዕን 2:18፤ 1ቆሮ 10:14
ዘሌ. 19:4ዘፀ 20:4, 23፤ ዘዳ 27:15
ዘሌ. 19:5ዘሌ 3:1
ዘሌ. 19:5ዘሌ 7:11, 12
ዘሌ. 19:6ዘሌ 7:17, 18
ዘሌ. 19:9ዘሌ 23:22፤ ዘዳ 24:19
ዘሌ. 19:10ዘዳ 15:7
ዘሌ. 19:11ዘፀ 20:15፤ ኤፌ 4:28
ዘሌ. 19:11ዘሌ 6:2፤ ምሳሌ 12:22፤ ኤፌ 4:25
ዘሌ. 19:12ዘፀ 20:7፤ ማቴ 5:33, 37፤ ያዕ 5:12
ዘሌ. 19:13ምሳሌ 22:16፤ ማር 10:19
ዘሌ. 19:13ምሳሌ 22:22
ዘሌ. 19:13ዘዳ 24:15፤ ኤር 22:13፤ ያዕ 5:4
ዘሌ. 19:14ዘዳ 27:18
ዘሌ. 19:14ዘሌ 25:17፤ ነህ 5:15፤ ምሳሌ 1:7፤ 8:13፤ 1ጴጥ 2:17
ዘሌ. 19:15ዘፀ 23:3፤ ዘዳ 1:16, 17፤ 16:19፤ 2ዜና 19:6፤ ሮም 2:11፤ ያዕ 2:9
ዘሌ. 19:16መዝ 15:1, 3
ዘሌ. 19:16ዘፀ 20:16፤ 1ነገ 21:13
ዘሌ. 19:17ምሳሌ 10:18፤ 1ዮሐ 2:9፤ 3:15
ዘሌ. 19:17መዝ 141:5፤ ምሳሌ 9:8፤ ማቴ 18:15
ዘሌ. 19:18ምሳሌ 20:22፤ ሮም 12:19
ዘሌ. 19:18ማቴ 5:43, 44፤ 22:39፤ ሮም 13:9፤ ገላ 5:14፤ ያዕ 2:8
ዘሌ. 19:19ዘዳ 22:9
ዘሌ. 19:19ዘዳ 22:11
ዘሌ. 19:21ዘሌ 6:6, 7
ዘሌ. 19:24ዘዳ 26:1, 2፤ ምሳሌ 3:9
ዘሌ. 19:26ዘሌ 3:17፤ 17:13፤ ዘዳ 12:23፤ ሥራ 15:20, 29
ዘሌ. 19:26ዘፀ 8:7፤ ዘዳ 18:10-12፤ ገላ 5:19, 20፤ ራእይ 21:8
ዘሌ. 19:27ዘሌ 21:1, 5
ዘሌ. 19:28ዘዳ 14:1
ዘሌ. 19:29ዕብ 13:4፤ 1ጴጥ 4:3
ዘሌ. 19:29ዘዳ 23:17
ዘሌ. 19:30ዘፀ 20:10፤ 31:13
ዘሌ. 19:31ዘሌ 20:6፤ ዘዳ 18:10-12፤ 1ዜና 10:13፤ ኢሳ 8:19
ዘሌ. 19:31ዘሌ 20:27፤ ሥራ 16:16
ዘሌ. 19:32ምሳሌ 16:31፤ 20:29
ዘሌ. 19:32ኢዮብ 32:6፤ ምሳሌ 23:22፤ 1ጢሞ 5:1
ዘሌ. 19:32ኢዮብ 28:28፤ ምሳሌ 1:7፤ 8:13፤ 1ጴጥ 2:17
ዘሌ. 19:33ዘፀ 23:9
ዘሌ. 19:34ዘፀ 12:49
ዘሌ. 19:34ዘፀ 22:21
ዘሌ. 19:35ዘዳ 25:13, 15፤ ምሳሌ 20:10
ዘሌ. 19:36ምሳሌ 11:1
ዘሌ. 19:37ዘሌ 18:5፤ ዘዳ 4:6
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
  • 32
  • 33
  • 34
  • 35
  • 36
  • 37
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘሌዋውያን 19:1-37

ዘሌዋውያን

19 በተጨማሪም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 2 “ለመላው የእስራኤል ማኅበረሰብ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ቅዱስ ስለሆንኩ እናንተም ቅዱስ ልትሆኑ ይገባል።+

3 “‘ከእናንተ እያንዳንዱ እናቱንና አባቱን ያክብር፤*+ ሰንበቶቼንም ይጠብቅ።+ እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ። 4 ከንቱ ወደሆኑ አማልክት ዞር አትበሉ፤+ ወይም ከቀለጠ ብረት ለራሳችሁ አማልክትን አትሥሩ።+ እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ።

5 “‘ለይሖዋ የኅብረት መሥዋዕት የምታቀርቡ+ ከሆነ ተቀባይነት በሚያስገኝላችሁ መንገድ አቅርቡት።+ 6 መሥዋዕቱም በዚያው ባቀረባችሁበት ዕለትና በቀጣዩ ቀን መበላት ይኖርበታል፤ ተርፎ እስከ ሦስተኛው ቀን የቆየ ካለ ግን በእሳት መቃጠል አለበት።+ 7 ይሁንና ከተረፈው ላይ በሦስተኛው ቀን ከተበላ ተቀባይነት የሌለው አስጸያፊ ነገር ይሆናል። 8 የበላውም ሰው የይሖዋን ቅዱስ ነገር ስላረከሰ በጥፋቱ ይጠየቃል፤ ያም ሰው* ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ መደረግ አለበት።

9 “‘የምድራችሁን አዝመራ በምትሰበስቡበት ጊዜ በእርሻችሁ ዳር ዳር ያለውን ሙልጭ አድርጋችሁ አትጨዱት፤ የእርሻችሁን ቃርሚያም አትልቀሙ።+ 10 በተጨማሪም በወይን እርሻህ ላይ የተረፈውን አትሰብስብ፤ በወይን እርሻህ ላይ የወዳደቀውን የወይን ፍሬ አትልቀም። እነዚህን ለድሃውና* ለባዕድ አገሩ ሰው ተውለት።+ እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ።

11 “‘አትስረቁ፤+ አታታሉ፤+ አንዳችሁ በሌላው ላይ ሐቀኝነት የጎደለው ድርጊት አትፈጽሙ። 12 በስሜ በሐሰት አትማሉ፤+ በዚህም የአምላካችሁን ስም አታርክሱ። እኔ ይሖዋ ነኝ። 13 ባልንጀራህን አታጭበርብር፤+ አትዝረፈውም።+ የቅጥር ሠራተኛውን ደሞዝ ሳትከፍል አታሳድር።+

14 “‘መስማት የተሳነውን አትርገም ወይም በዓይነ ስውሩ ፊት እንቅፋት አታስቀምጥ፤+ አምላክህን ፍራ።+ እኔ ይሖዋ ነኝ።

15 “‘ፍርድ አታዛቡ። ለድሃው አታዳላ ወይም ባለጸጋውን ከሌሎች አስበልጠህ አትመልከት።+ ለባልንጀራህ ፍትሐዊ ፍርድ ፍረድ።

16 “‘በሕዝብህ መካከል እየዞርክ ስም አታጥፋ።+ በባልንጀራህ ሕይወት* ላይ አትነሳ።*+ እኔ ይሖዋ ነኝ።

17 “‘ወንድምህን በልብህ አትጥላው።+ የባልንጀራህ ኃጢአት ተባባሪ እንዳትሆን ተግሣጽ በሚያስፈልገው ጊዜ ሁሉ ገሥጸው።+

18 “‘የሕዝብህን ልጆች አትበቀል፤+ በእነሱም ላይ ቂም አትያዝ፤ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ።+ እኔ ይሖዋ ነኝ።

19 “‘የሚከተሉትን ደንቦቼን ጠብቁ፦ ሁለት ዓይነት እንስሳትን አታዳቅል። በእርሻህ ላይ ሁለት ዓይነት ዘር አትዝራ፤+ ከሁለት የተለያዩ የክር ዓይነቶች የተሠራ ልብስ አትልበስ።+

20 “‘አንድ ወንድ ከአንዲት ሴት ጋር ቢተኛና ከእሷ ጋር የፆታ ግንኙነት ቢፈጽም፣ ሴቲቱ ደግሞ ለሌላ ወንድ የታጨች ሆኖም ገና ያልተዋጀች ወይም ነፃ ያልወጣች ባሪያ ብትሆን የቅጣት እርምጃ መወሰድ አለበት። ይሁንና ይህች ሴት ገና ነፃ ስላልወጣች መገደል የለባቸውም። 21 ሰውየው የበደል መባውን ይኸውም ለበደል መባ የሚሆነውን አውራ በግ ወደ ይሖዋ ወደ መገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ያምጣ።+ 22 ካህኑም ሰውየው ለሠራው ኃጢአት የበደል መባ እንዲሆን በቀረበው አውራ በግ በይሖዋ ፊት ያስተሰርይለታል፤ የሠራውም ኃጢአት ይቅር ይባልለታል።

23 “‘እናንተም ወደ ምድሪቱ ብትገቡና ለምግብ የሚሆን ዛፍ ብትተክሉ ፍሬውን ርኩስና የተከለከለ* አድርጋችሁ ቁጠሩት። ለሦስት ዓመት ከእሱ መብላት የለባችሁም።* ፍሬው መበላት የለበትም። 24 በአራተኛው ዓመት ግን ፍሬው በሙሉ በይሖዋ ፊት የምትደሰቱበት ቅዱስ ነገር ይሆናል።+ 25 ከዚያም በአምስተኛው ዓመት ፍሬውን መብላት ትችላላችሁ፤ ይህን ካደረጋችሁ ምርታችሁ ይበዛላችኋል። እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ።

26 “‘ደም ያለበትን ማንኛውንም ነገር አትብሉ።+

“‘አታስጠንቁሉ ወይም አስማት አትሥሩ።+

27 “‘ጆሮ ግንዳችሁ አካባቢ ያለውን ፀጉር አትላጩ* ወይም የጢማችሁን ዳር ዳር አትላጩ።+

28 “‘ለሞተ ሰው* ብላችሁ አካላችሁን አትተልትሉ+ ወይም ሰውነታችሁን አትነቀሱ። እኔ ይሖዋ ነኝ።

29 “‘ምድሪቱ ዝሙት እንዳትፈጽምና ልቅ በሆነ ምግባር እንዳትሞላ+ ሴት ልጅህን ዝሙት አዳሪ በማድረግ አታዋርዳት።+

30 “‘ሰንበቶቼን ጠብቁ፤+ ለመቅደሴ አክብሮት* ይኑራችሁ። እኔ ይሖዋ ነኝ።

31 “‘ወደ መናፍስት ጠሪዎች አትሂዱ፤+ ጠንቋዮችንም አትጠይቁ፤+ እንዲህ ካደረጋችሁ በእነሱ ትረክሳላችሁ። እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ።

32 “‘በሸበተው ሰው ፊት ተነስ፤+ አረጋዊውንም አክብር፤+ አምላክህን ፍራ።+ እኔ ይሖዋ ነኝ።

33 “‘በምድራችሁ አብሯችሁ የሚኖር የባዕድ አገር ሰው ካለ አትበድሉት።+ 34 አብሯችሁ የሚኖረውን የባዕድ አገር ሰው እንደ አገራችሁ ተወላጅ አድርጋችሁ ተመልከቱት፤+ እንደ ራሳችሁ አድርጋችሁም ውደዱት፤ ምክንያቱም እናንተም በግብፅ ምድር ሳላችሁ የባዕድ አገር ሰው ነበራችሁ።+ እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ።

35 “‘ርዝመትን፣ ክብደትን ወይም መጠንን ስትለኩ በተጭበረበረ መለኪያ አትጠቀሙ።+ 36 ትክክለኛ ሚዛን፣ ትክክለኛ የሚዛን ድንጋዮች፣ ትክክለኛ የደረቅ ነገር መስፈሪያና* ትክክለኛ የፈሳሽ ነገር መለኪያ* ሊኖራችሁ ይገባል።+ ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ። 37 ስለሆነም ደንቦቼን ሁሉና ድንጋጌዎቼን በሙሉ ጠብቁ፤ እንዲሁም ፈጽሟቸው።+ እኔ ይሖዋ ነኝ።’”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ