ዘሌዋውያን 27:30 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 30 “‘እርሻው ከሚሰጠው ምርትም ሆነ ዛፉ ከሚያፈራው ፍሬ ውስጥ የምድሩ አንድ አሥረኛ*+ ሁሉ የይሖዋ ነው። ይህ ለይሖዋ የተቀደሰ ነው። ነህምያ 10:37 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 37 ከዚህም በተጨማሪ የተፈጨውን የእህላችንን በኩር፣+ መዋጮዎቻችንን፣ ማንኛውም ዛፍ የሚያፈራውን ፍሬ፣+ አዲስ የወይን ጠጅና ዘይት+ ወደ አምላካችን ቤት ግምጃ ቤቶች*+ ወደ ካህናቱ እናመጣለን፤ እንዲሁም ከእርሻ ከተሞቻችን ሁሉ አንድ አሥረኛውን* የሚቀበሉት ሌዋውያኑ ስለሆኑ የመሬታችንን አንድ አሥረኛ ለሌዋውያኑ እናመጣለን።+ ነህምያ 12:44 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 44 በዚያን ቀን መዋጮዎች፣+ የእህል በኩራትና+ አሥራት+ በሚቀመጡባቸው ግምጃ ቤቶች+ ላይ ሰዎች ተሾሙ። እነሱም በሕጉ ላይ በታዘዘው መሠረት ለካህናቱና ለሌዋውያኑ የሚሰጠውን ድርሻ ከየከተሞቹ እርሻዎች እየሰበሰቡ ወደዚያ ማስገባት ነበረባቸው፤+ ምክንያቱም በሚያገለግሉት ካህናትና ሌዋውያን+ የተነሳ በይሁዳ ውስጥ ታላቅ ደስታ ነበር። ዕብራውያን 7:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 እርግጥ የክህነት ኃላፊነት የሚቀበሉ ከሌዊ ልጆች ወገን የሆኑት ሰዎች+ ምንም እንኳ ወንድሞቻቸው የአብርሃም ዘሮች ቢሆኑም ከሕዝቡ ማለትም ከገዛ ወንድሞቻቸው አሥራት እንዲሰበስቡ ሕጉ ያዛል።+
37 ከዚህም በተጨማሪ የተፈጨውን የእህላችንን በኩር፣+ መዋጮዎቻችንን፣ ማንኛውም ዛፍ የሚያፈራውን ፍሬ፣+ አዲስ የወይን ጠጅና ዘይት+ ወደ አምላካችን ቤት ግምጃ ቤቶች*+ ወደ ካህናቱ እናመጣለን፤ እንዲሁም ከእርሻ ከተሞቻችን ሁሉ አንድ አሥረኛውን* የሚቀበሉት ሌዋውያኑ ስለሆኑ የመሬታችንን አንድ አሥረኛ ለሌዋውያኑ እናመጣለን።+
44 በዚያን ቀን መዋጮዎች፣+ የእህል በኩራትና+ አሥራት+ በሚቀመጡባቸው ግምጃ ቤቶች+ ላይ ሰዎች ተሾሙ። እነሱም በሕጉ ላይ በታዘዘው መሠረት ለካህናቱና ለሌዋውያኑ የሚሰጠውን ድርሻ ከየከተሞቹ እርሻዎች እየሰበሰቡ ወደዚያ ማስገባት ነበረባቸው፤+ ምክንያቱም በሚያገለግሉት ካህናትና ሌዋውያን+ የተነሳ በይሁዳ ውስጥ ታላቅ ደስታ ነበር።
5 እርግጥ የክህነት ኃላፊነት የሚቀበሉ ከሌዊ ልጆች ወገን የሆኑት ሰዎች+ ምንም እንኳ ወንድሞቻቸው የአብርሃም ዘሮች ቢሆኑም ከሕዝቡ ማለትም ከገዛ ወንድሞቻቸው አሥራት እንዲሰበስቡ ሕጉ ያዛል።+