ዘፍጥረት 14:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 የሚጨቁኑህን በእጅህ አሳልፎ የሰጠህ፣ልዑሉ አምላክ ይወደስ!” አብራምም ከሁሉም ነገር ላይ አንድ አሥረኛውን ሰጠው።+ ዘፍጥረት 28:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 እንደ ዓምድ ያቆምኩት ይህ ድንጋይም የአምላክ ቤት ይሆናል፤+ አምላክ ሆይ፣ እኔም ከምትሰጠኝ ከማንኛውም ነገር አንድ አሥረኛውን ለአንተ እሰጣለሁ።” ዘኁልቁ 18:21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 “እንግዲህ የሌዊ ወንዶች ልጆች ለሚያከናውኑት አገልግሎት ይኸውም በመገናኛ ድንኳኑ ለሚሰጡት አገልግሎት በእስራኤል ውስጥ ያለውን የማንኛውንም ነገር አንድ አሥረኛ ውርሻ አድርጌ እንደሰጠኋቸው+ ልብ በል። ዘኁልቁ 18:26 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 26 “ሌዋውያኑን እንዲህ በላቸው፦ ‘ከእስራኤላውያን ላይ ውርሻችሁ አድርጌ የሰጠኋችሁን አንድ አሥረኛ ከእነሱ እጅ ትቀበላላችሁ፤+ እናንተ ደግሞ የአንድ አሥረኛውን አንድ አሥረኛ ለይሖዋ መዋጮ አድርጋችሁ ትሰጣላችሁ።+ ዘዳግም 14:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 “በየዓመቱ ከእርሻህ ላይ ከምታገኘው ምርት ሁሉ አንድ አሥረኛውን* መስጠት አለብህ።+ 2 ዜና መዋዕል 31:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ትእዛዙ እንደወጣ እስራኤላውያን የእህሉን፣ የአዲሱን የወይን ጠጅ፣ የዘይቱን፣+ የማሩንና የእርሻውን ፍሬ+ ሁሉ በኩራት በብዛት ሰጡ፤ ከእያንዳንዱም ነገር ላይ አንድ አሥረኛውን አትረፍርፈው አመጡ።+ ነህምያ 13:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 የይሁዳ ሰዎችም ሁሉ የእህሉን፣ የአዲሱን የወይን ጠጅና የዘይቱን አንድ አሥረኛ+ ወደ ግምጃ ቤቶቹ አስገቡ።+ ሚልክያስ 3:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 በቤቴ ውስጥ እህል እንዲኖር አሥራቱን* ሁሉ ወደ ጎተራው አስገቡ”+ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤ “የሰማያትን መስኮቶች ከፍቼ+ ማስቀመጫ እስክታጡ ድረስ የተትረፈረፈ በረከት ባላፈስላችሁ፣*+ እስቲ በዚህ ፈትኑኝ።” ሉቃስ 11:42 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 42 እናንተ ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! ምክንያቱም ከኮሰረት፣ ከጤና አዳምና ከሌሎች አትክልቶች ሁሉ አሥራት ትሰጣላችሁ፤+ ነገር ግን የአምላክን ፍትሕና እሱን መውደድን ችላ ትላላችሁ። እርግጥ አሥራት የመስጠት ግዴታ አለባችሁ፤ ሆኖም ሌሎቹን ነገሮች ችላ ማለት አልነበረባችሁም።+ ዕብራውያን 7:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 እርግጥ የክህነት ኃላፊነት የሚቀበሉ ከሌዊ ልጆች ወገን የሆኑት ሰዎች+ ምንም እንኳ ወንድሞቻቸው የአብርሃም ዘሮች ቢሆኑም ከሕዝቡ ማለትም ከገዛ ወንድሞቻቸው አሥራት እንዲሰበስቡ ሕጉ ያዛል።+
21 “እንግዲህ የሌዊ ወንዶች ልጆች ለሚያከናውኑት አገልግሎት ይኸውም በመገናኛ ድንኳኑ ለሚሰጡት አገልግሎት በእስራኤል ውስጥ ያለውን የማንኛውንም ነገር አንድ አሥረኛ ውርሻ አድርጌ እንደሰጠኋቸው+ ልብ በል።
26 “ሌዋውያኑን እንዲህ በላቸው፦ ‘ከእስራኤላውያን ላይ ውርሻችሁ አድርጌ የሰጠኋችሁን አንድ አሥረኛ ከእነሱ እጅ ትቀበላላችሁ፤+ እናንተ ደግሞ የአንድ አሥረኛውን አንድ አሥረኛ ለይሖዋ መዋጮ አድርጋችሁ ትሰጣላችሁ።+
5 ትእዛዙ እንደወጣ እስራኤላውያን የእህሉን፣ የአዲሱን የወይን ጠጅ፣ የዘይቱን፣+ የማሩንና የእርሻውን ፍሬ+ ሁሉ በኩራት በብዛት ሰጡ፤ ከእያንዳንዱም ነገር ላይ አንድ አሥረኛውን አትረፍርፈው አመጡ።+
10 በቤቴ ውስጥ እህል እንዲኖር አሥራቱን* ሁሉ ወደ ጎተራው አስገቡ”+ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤ “የሰማያትን መስኮቶች ከፍቼ+ ማስቀመጫ እስክታጡ ድረስ የተትረፈረፈ በረከት ባላፈስላችሁ፣*+ እስቲ በዚህ ፈትኑኝ።”
42 እናንተ ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! ምክንያቱም ከኮሰረት፣ ከጤና አዳምና ከሌሎች አትክልቶች ሁሉ አሥራት ትሰጣላችሁ፤+ ነገር ግን የአምላክን ፍትሕና እሱን መውደድን ችላ ትላላችሁ። እርግጥ አሥራት የመስጠት ግዴታ አለባችሁ፤ ሆኖም ሌሎቹን ነገሮች ችላ ማለት አልነበረባችሁም።+
5 እርግጥ የክህነት ኃላፊነት የሚቀበሉ ከሌዊ ልጆች ወገን የሆኑት ሰዎች+ ምንም እንኳ ወንድሞቻቸው የአብርሃም ዘሮች ቢሆኑም ከሕዝቡ ማለትም ከገዛ ወንድሞቻቸው አሥራት እንዲሰበስቡ ሕጉ ያዛል።+