ዘፀአት 16:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 እስራኤላውያንም ባዩት ጊዜ ምን እንደሆነ ስላላወቁ እርስ በርሳቸው “ይህ ነገር ምንድን ነው?” ይባባሉ ጀመር። ስለሆነም ሙሴ እንዲህ አላቸው፦ “ይሖዋ እንድትበሉት የሰጣችሁ ምግብ ነው።+ ዘኁልቁ 11:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 አሁን ግን ዝለናል።* ከዚህ መና በስተቀር ሌላ የምናየው ነገር የለም።”+ መዝሙር 78:24, 25 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 የሚበሉት መና አዘነበላቸው፤የሰማይንም እህል ሰጣቸው።+ 25 ሰዎች የኃያላንን*+ ምግብ በሉ፤እስኪጠግቡ ድረስ እንዲበሉ በቂ ምግብ አቀረበላቸው።+
15 እስራኤላውያንም ባዩት ጊዜ ምን እንደሆነ ስላላወቁ እርስ በርሳቸው “ይህ ነገር ምንድን ነው?” ይባባሉ ጀመር። ስለሆነም ሙሴ እንዲህ አላቸው፦ “ይሖዋ እንድትበሉት የሰጣችሁ ምግብ ነው።+