ዘፀአት 13:21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 ይሖዋ የሚሄዱበትን መንገድ ይመራቸው ዘንድ ቀን ቀን በደመና ዓምድ ውስጥ ሆኖ ከፊት ከፊታቸው ይሄድ ነበር፤+ ሌሊት ሌሊት ደግሞ ብርሃን እንዲያገኙ ለማድረግ በእሳት ዓምድ ውስጥ ሆኖ ይመራቸው ነበር፤+ በመሆኑም ቀንም ሆነ ሌሊት ይጓዙ ነበር። ዘፀአት 23:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 “በመንገድ ላይ እንዲጠብቅህና ወዳዘጋጀሁት ስፍራ እንዲያመጣህ በፊትህ መልአክ እልካለሁ።+ ዘፀአት 29:45 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 45 እኔም በእስራኤል ሕዝብ መካከል እኖራለሁ፤* አምላካቸውም እሆናለሁ።+ ኢሳይያስ 8:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 ዕቅድ አውጡ፤ ይሁንና ይጨናገፋል! የፈለጋችሁትን ተናገሩ፤ ሆኖም አይሳካም፤አምላክ ከእኛ ጋር ነውና!*+
21 ይሖዋ የሚሄዱበትን መንገድ ይመራቸው ዘንድ ቀን ቀን በደመና ዓምድ ውስጥ ሆኖ ከፊት ከፊታቸው ይሄድ ነበር፤+ ሌሊት ሌሊት ደግሞ ብርሃን እንዲያገኙ ለማድረግ በእሳት ዓምድ ውስጥ ሆኖ ይመራቸው ነበር፤+ በመሆኑም ቀንም ሆነ ሌሊት ይጓዙ ነበር።