ዘኁልቁ 11:28 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 28 በዚህ ጊዜ ከወጣትነቱ ጀምሮ የሙሴ አገልጋይ የነበረው የነዌ ልጅ ኢያሱ+ “ጌታዬ ሙሴ ሆይ፣ እነዚህን ሰዎች ከልክላቸው እንጂ!”+ ሲል ተናገረ። ዘኁልቁ 14:30 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 30 ከየፎኒ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በስተቀር+ አንዳችሁም ብትሆኑ በዚያ እንደማኖራችሁ ወደማልኩላችሁ* ምድር አትገቡም።+ ዘኁልቁ 27:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 በመሆኑም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “መንፈስ ያለበትን የነዌን ልጅ ኢያሱን ወስደህ እጅህን ጫንበት።+