የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘዳግም 30:1-3
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 30 “ይህ ቃል ሁሉ ይኸውም በፊትህ ያስቀመጥኩት በረከትና እርግማን+ በአንተ ላይ በሚመጣበትና አምላክህ ይሖዋ በመካከላቸው እንድትበተን ባደረገህ ብሔራት ምድር+ ሆነህ ይህን ቃል ሁሉ በምታስታውስበት* ጊዜ+ 2 እንዲሁም አንተም ሆንክ ልጆችህ እኔ ዛሬ በማዝህ ትእዛዝ ሁሉ መሠረት በሙሉ ልባችሁና በሙሉ ነፍሳችሁ*+ ወደ አምላካችሁ ወደ ይሖዋ በምትመለሱበትና ቃሉን በምትሰሙበት ጊዜ+ 3 አምላክህ ይሖዋ ተማርከው የተወሰዱብህን ይመልስልሃል፤+ ምሕረትም ያሳይሃል፤+ እንዲሁም አምላክህ ይሖዋ በመካከላቸው እንድትበተን ካደረገህ ሕዝቦች ምድር ሁሉ መልሶ ይሰበስብሃል።+

  • ዘዳግም 30:8-10
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 8 “አንተም ተመልሰህ የይሖዋን ቃል ትሰማለህ፤ እኔ ዛሬ የማዝህን ትእዛዛቱን ሁሉ ትፈጽማለህ። 9 አምላክህ ይሖዋ በአባቶችህ ደስ እንደተሰኘ+ ሁሉ ይሖዋ አንተንም በማበልጸግ ስለሚደሰት የሆድህን ፍሬ፣ እንስሶችህንና የምድርህን ፍሬ በማብዛት በእጅህ ሥራ ሁሉ እጅግ እንድትበለጽግ ያደርግሃል።+ 10 ይህም የሚሆነው የአምላክህን የይሖዋን ቃል ስለምትሰማ፣ በዚህ የሕግ መጽሐፍ የተጻፉትን ትእዛዛቱንና ደንቦቹን ስለምትጠብቅ እንዲሁም በሙሉ ልብህና በሙሉ ነፍስህ* ወደ አምላክህ ወደ ይሖዋ ስለምትመለስ ነው።+

  • 1 ነገሥት 8:48, 49
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 48 ማርከው በወሰዷቸው ጠላቶቻቸውም ምድር ሆነው በሙሉ ልባቸውና በሙሉ ነፍሳቸው* ወደ አንተ ቢመለሱ+ እንዲሁም ለአባቶቻቸው በሰጠሃቸው ምድር፣ አንተ በመረጥካት ከተማና ለስምህ በሠራሁት ቤት አቅጣጫ ወደ አንተ ቢጸልዩ+ 49 ጸሎታቸውንና ሞገስ ለማግኘት ያቀረቡትን ልመና ከመኖሪያ ቦታህ ከሰማያት ሆነህ+ ስማ፤ ፍረድላቸውም፤

  • ኤርምያስ 29:13
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 13 “‘እኔን ትሻላችሁ፤ በሙሉ ልባችሁ ስለምትፈልጉኝ ታገኙኛላችሁ።+

  • ኢዩኤል 2:12
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 12 “አሁንም ቢሆን” ይላል ይሖዋ፣

      “በጾም፣+ በለቅሶና በዋይታ በሙሉ ልባችሁ ወደ እኔ ተመለሱ።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ