ምሳሌ 4:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 አባቴ እንዲህ ሲል አስተማረኝ፦ “ልብህ ቃሌን አጥብቆ ይያዝ።+ ትእዛዛቴን ጠብቅ፤ በሕይወትም ትኖራለህ።+ መክብብ 12:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ሁሉ ነገር ከተሰማ በኋላ መደምደሚያው ይህ ነው፦ እውነተኛውን አምላክ ፍራ፤+ ትእዛዛቱንም ጠብቅ፤+ ይህ የሰው አጠቃላይ ግዴታ ነውና።+ ኢሳይያስ 48:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 ትእዛዛቴን ብትሰማ ምንኛ መልካም ነው!+ እንዲህ ብታደርግ ሰላምህ እንደ ወንዝ፣+ጽድቅህም እንደ ባሕር ሞገድ ይሆናል።+ 1 ዮሐንስ 5:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 አምላክን መውደድ ማለት ትእዛዛቱን መጠበቅ ማለት ነውና፤+ ትእዛዛቱ ደግሞ ከባድ አይደሉም፤+