ዘዳግም 11:25 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 25 ማንም ሰው ሊቋቋማችሁ አይችልም።+ አምላካችሁ ይሖዋም ቃል በገባላችሁ መሠረት በምትረግጡት ምድር ሁሉ ላይ ሽብርና ፍርሃት ይለቃል።+ ኢያሱ 1:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 በሕይወት ዘመንህ ሁሉ ማንም አይቋቋምህም።+ ከሙሴ ጋር እንደነበርኩ ሁሉ ከአንተም ጋር እሆናለሁ።+ አልጥልህም ወይም አልተውህም።+ ሮም 8:31 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 31 እንግዲህ ስለ እነዚህ ነገሮች ምን እንበል? አምላክ ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ሊቃወመን ይችላል?+