ዘሌዋውያን 19:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 “ለመላው የእስራኤል ማኅበረሰብ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ቅዱስ ስለሆንኩ እናንተም ቅዱስ ልትሆኑ ይገባል።+ ዘሌዋውያን 20:26 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 26 እኔ ይሖዋ ቅዱስ ስለሆንኩ እናንተም ለእኔ ቅዱስ ልትሆኑ ይገባል፤+ የእኔ ትሆኑ ዘንድ ከሌሎች ሕዝቦች ለየኋችሁ።+ ዘዳግም 28:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 የአምላክህን የይሖዋን ትእዛዛት ከጠበቅክና በመንገዶቹ ከሄድክ ይሖዋ በማለልህ መሠረት+ ለእሱ ቅዱስ ሕዝብ አድርጎ ያቆምሃል።+ 1 ጴጥሮስ 1:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 ከዚህ ይልቅ የጠራችሁ ቅዱስ አምላክ፣ ቅዱስ እንደሆነ ሁሉ እናንተም በምግባራችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ፤+