ዘፀአት 23:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 “ጉቦ አትቀበል፤ ምክንያቱም ጉቦ አጥርተው የሚያዩ ሰዎችን ዓይን ያሳውራል፤ እንዲሁም የጻድቅ ሰዎችን ቃል ሊያዛባ ይችላል።+ 1 ሳሙኤል 12:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 አሁንም ያለሁት በፊታችሁ ነው። እስቲ የምከሰስበት ነገር ካለ በይሖዋና እሱ በቀባው+ ፊት ንገሩኝ፦ የማንን በሬ ወይም የማንን አህያ ወስጃለሁ?+ ወይስ ማንን አታልያለሁ? ደግሞስ በማን ላይ ግፍ ፈጽሜአለሁ? አይቼ እንዳላየሁ ለመሆንስ ከማን እጅ ጉቦ ተቀብያለሁ?+ እንዲህ አድርጌ ከሆነ እመልስላችኋለሁ።”+ መክብብ 7:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ግፍ ጥበበኛውን ሊያሳብደው ይችላል፤ ጉቦም ልብን ያበላሻል።+
3 አሁንም ያለሁት በፊታችሁ ነው። እስቲ የምከሰስበት ነገር ካለ በይሖዋና እሱ በቀባው+ ፊት ንገሩኝ፦ የማንን በሬ ወይም የማንን አህያ ወስጃለሁ?+ ወይስ ማንን አታልያለሁ? ደግሞስ በማን ላይ ግፍ ፈጽሜአለሁ? አይቼ እንዳላየሁ ለመሆንስ ከማን እጅ ጉቦ ተቀብያለሁ?+ እንዲህ አድርጌ ከሆነ እመልስላችኋለሁ።”+