ኢያሱ 6:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 ከተማዋም ሆነች በውስጧ ያለው ነገር ሁሉ ሙሉ በሙሉ መጥፋት አለበት፤+ ከተማዋ ሙሉ በሙሉ የይሖዋ ነች። በሕይወት የሚተርፉት ዝሙት አዳሪዋ ረዓብና+ ከእሷ ጋር በቤቱ ውስጥ ያሉት ብቻ ናቸው፤ ምክንያቱም እሷ የላክናቸውን መልእክተኞች ደብቃለች።+ ኢያሱ 10:28 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 28 ኢያሱም በዚያን ዕለት መቄዳን+ በመቆጣጠር ሕዝቡን በሰይፍ ፈጀ። ንጉሥዋንና በውስጧ ያለውን ሰው* ሁሉ አንድም ሳያስቀር ፈጽሞ አጠፋ።+ በኢያሪኮ ንጉሥ ላይ እንዳደረገውም ሁሉ በመቄዳ ንጉሥ+ ላይ አደረገ። ኢያሱ 11:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 እነሱም በውስጧ ያለውን ሰው* ሁሉ በሰይፍ በመምታት ፈጽመው አጠፉ።+ እስትንፋስ ያለው አንድም ነገር አላስቀሩም።+ ከዚያም ሃጾርን በእሳት አቃጠላት።
17 ከተማዋም ሆነች በውስጧ ያለው ነገር ሁሉ ሙሉ በሙሉ መጥፋት አለበት፤+ ከተማዋ ሙሉ በሙሉ የይሖዋ ነች። በሕይወት የሚተርፉት ዝሙት አዳሪዋ ረዓብና+ ከእሷ ጋር በቤቱ ውስጥ ያሉት ብቻ ናቸው፤ ምክንያቱም እሷ የላክናቸውን መልእክተኞች ደብቃለች።+
28 ኢያሱም በዚያን ዕለት መቄዳን+ በመቆጣጠር ሕዝቡን በሰይፍ ፈጀ። ንጉሥዋንና በውስጧ ያለውን ሰው* ሁሉ አንድም ሳያስቀር ፈጽሞ አጠፋ።+ በኢያሪኮ ንጉሥ ላይ እንዳደረገውም ሁሉ በመቄዳ ንጉሥ+ ላይ አደረገ።