ሮም 13:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 መረን በለቀቀ ፈንጠዝያና በስካር፣ ልቅ በሆነ የፆታ ግንኙነትና ማንአለብኝነት በሚንጸባረቅበት ድርጊት*+ እንዲሁም በጠብና በቅናት+ ሳይሆን በቀን ብርሃን እንደምንመላለስ በጨዋነት እንመላለስ።+ 1 ቆሮንቶስ 6:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 ወይም ሌቦች ወይም ስግብግቦች+ ወይም ሰካራሞች+ ወይም ተሳዳቢዎች ወይም ቀማኞች የአምላክን መንግሥት አይወርሱም።+ ኤፌሶን 5:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 በተጨማሪም መረን ለለቀቀ ሕይወት* ስለሚዳርጋችሁ በወይን ጠጅ አትስከሩ፤+ ከዚህ ይልቅ በመንፈስ መሞላታችሁን ቀጥሉ።
13 መረን በለቀቀ ፈንጠዝያና በስካር፣ ልቅ በሆነ የፆታ ግንኙነትና ማንአለብኝነት በሚንጸባረቅበት ድርጊት*+ እንዲሁም በጠብና በቅናት+ ሳይሆን በቀን ብርሃን እንደምንመላለስ በጨዋነት እንመላለስ።+