ዘፀአት 18:21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 ሆኖም ከመላው ሕዝብ መካከል አምላክን የሚፈሩትንና ብቃት ያላቸውን+ እንዲሁም አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት የማይፈልጉትንና እምነት የሚጣልባቸውን ሰዎች+ ምረጥ፤ እነዚህንም የሺህ አለቆች፣ የመቶ አለቆች፣ የሃምሳ አለቆችና የአሥር አለቆች አድርገህ በሕዝቡ ላይ ሹማቸው።+ ዘዳግም 1:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ከየነገዶቻችሁ ጥበበኛና አስተዋይ የሆኑ እንዲሁም ተሞክሮ ያካበቱ ወንዶችን ምረጡ፤ እኔም በእናንተ ላይ መሪ አድርጌ እሾማቸዋለሁ።’+ ዘዳግም 16:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 “አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህ ከተሞች ሁሉ ለእያንዳንዱ ነገድ ዳኞችንና አለቆችን ሹም፤+ እነሱም ለሕዝቡ የጽድቅ ፍርድ ይፍረዱ።
21 ሆኖም ከመላው ሕዝብ መካከል አምላክን የሚፈሩትንና ብቃት ያላቸውን+ እንዲሁም አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት የማይፈልጉትንና እምነት የሚጣልባቸውን ሰዎች+ ምረጥ፤ እነዚህንም የሺህ አለቆች፣ የመቶ አለቆች፣ የሃምሳ አለቆችና የአሥር አለቆች አድርገህ በሕዝቡ ላይ ሹማቸው።+