ዘሌዋውያን 26:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 “‘እኔም ሞገስ አሳያችኋለሁ፤* ፍሬያማ እንድትሆኑና እንድትበዙ አደርጋችኋለሁ፤+ ከእናንተ ጋር የገባሁትንም ቃል ኪዳኔን እጠብቃለሁ።+ መዝሙር 127:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 እነሆ፣ ልጆች* ከይሖዋ የተገኙ ውርሻ ናቸው፤+የማህፀንም ፍሬ ከእሱ የሚገኝ ስጦታ ነው።+ መዝሙር 128:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ሚስትህ በቤትህ ውስጥ፣ ፍሬ እንደሚያፈራ ወይን ትሆናለች፤+ወንዶች ልጆችህ በማዕድህ ዙሪያ እንደ ወይራ ዛፍ ቡቃያዎች ይሆናሉ።