ዘፍጥረት 41:51, 52 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 51 ዮሴፍም “አምላክ የደረሰብኝን ችግር ሁሉና የአባቴን ቤት በሙሉ እንድረሳ አደረገኝ” በማለት ለበኩር ልጁ ምናሴ*+ የሚል ስም አወጣለት። 52 ሁለተኛውን ልጁን ደግሞ “መከራዬን ባየሁበት ምድር አምላክ ፍሬያማ አደረገኝ”+ በማለት ኤፍሬም*+ የሚል ስም አወጣለት። ዘሌዋውያን 26:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 “‘እኔም ሞገስ አሳያችኋለሁ፤* ፍሬያማ እንድትሆኑና እንድትበዙ አደርጋችኋለሁ፤+ ከእናንተ ጋር የገባሁትንም ቃል ኪዳኔን እጠብቃለሁ።+ ኢዮብ 42:12, 13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 በመሆኑም ይሖዋ ከፊተኛው የኢዮብ ሕይወት ይልቅ የኋለኛውን አብዝቶ ባረከ፤+ ኢዮብም 14,000 በጎች፣ 6,000 ግመሎች፣ 1,000 ጥማድ ከብቶችና 1,000 እንስት አህዮች አገኘ።+ 13 ደግሞም ሌሎች ሰባት ወንዶችና ሦስት ሴቶች ልጆች ወለደ።+ መዝሙር 128:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ሚስትህ በቤትህ ውስጥ፣ ፍሬ እንደሚያፈራ ወይን ትሆናለች፤+ወንዶች ልጆችህ በማዕድህ ዙሪያ እንደ ወይራ ዛፍ ቡቃያዎች ይሆናሉ።
51 ዮሴፍም “አምላክ የደረሰብኝን ችግር ሁሉና የአባቴን ቤት በሙሉ እንድረሳ አደረገኝ” በማለት ለበኩር ልጁ ምናሴ*+ የሚል ስም አወጣለት። 52 ሁለተኛውን ልጁን ደግሞ “መከራዬን ባየሁበት ምድር አምላክ ፍሬያማ አደረገኝ”+ በማለት ኤፍሬም*+ የሚል ስም አወጣለት።
12 በመሆኑም ይሖዋ ከፊተኛው የኢዮብ ሕይወት ይልቅ የኋለኛውን አብዝቶ ባረከ፤+ ኢዮብም 14,000 በጎች፣ 6,000 ግመሎች፣ 1,000 ጥማድ ከብቶችና 1,000 እንስት አህዮች አገኘ።+ 13 ደግሞም ሌሎች ሰባት ወንዶችና ሦስት ሴቶች ልጆች ወለደ።+