ዘዳግም 7:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 ሆኖም አትፍራቸው።+ አምላክህ ይሖዋ በፈርዖንና በግብፅ ሁሉ ላይ ያደረገውን አስታውስ፤+ ዘዳግም 31:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 በፊትህ የሚሄደው ይሖዋ ነው፤ እሱ ምንጊዜም ከአንተ ጋር ይሆናል።+ አይጥልህም ወይም አይተውህም። አትፍራ ወይም አትሸበር።”+ ኢያሱ 1:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ደፋርና ብርቱ ሁን ብዬ አዝዤህ አልነበረም? አምላክህ ይሖዋ በምትሄድበት ሁሉ ከአንተ ጋር ስለሆነ አትሸበር፤ አትፍራ።”+ ኢሳይያስ 12:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 እነሆ፣ አምላክ አዳኜ ነው!+ በእሱ እታመናለሁ፤ ምንም የሚያስፈራኝ ነገር የለም፤+ያህ* ይሖዋ ብርታቴና ኃይሌ ነው፤ለእኔም አዳኝ ሆኖልኛል።”+ ሮም 8:31 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 31 እንግዲህ ስለ እነዚህ ነገሮች ምን እንበል? አምላክ ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ሊቃወመን ይችላል?+