16 አምላክህ ይሖዋ ርስት አድርጎ በሚሰጥህ እነዚህ ሕዝቦች በሚኖሩባቸው ከተሞች ውስጥ ግን እስትንፋስ ያለውን ማንኛውንም ነገር በሕይወት አታስቀር።+ 17 ከዚህ ይልቅ አምላክህ ይሖዋ ባዘዘህ መሠረት ሂታውያንን፣ አሞራውያንን፣ ከነአናውያንን፣ ፈሪዛውያንን፣ ሂዋውያንንና ኢያቡሳውያንን ሙሉ በሙሉ አጥፋ፤+ 18 ይህን የምታደርጉት ለአማልክታቸው የሚያደርጓቸውን አስጸያፊ ነገሮች በሙሉ እንዳያስተምሯችሁና በአምላካችሁ በይሖዋ ላይ ኃጢአት እንድትሠሩ እንዳያደርጓችሁ ነው።+