የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኢያሱ 10:36, 37
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 36 ከዚያም ኢያሱና ከእሱ ጋር የነበሩት እስራኤላውያን በሙሉ ከኤግሎን ወደ ኬብሮን+ በመውጣት ኬብሮንን ወጓት። 37 እሷንም ተቆጣጥረው ከተማዋን፣ ንጉሥዋንና በዙሪያዋ ያሉትን አነስተኛ ከተሞች እንዲሁም በውስጧ ያለውን ሰው* ሁሉ አንድም ሳያስቀሩ በሰይፍ መቱ። በኤግሎንም ላይ እንዳደረገው ሁሉ ከተማዋንና በውስጧ ያለውን ሰው* ሁሉ ሙሉ በሙሉ አጠፋ።

  • ኢያሱ 15:13
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 13 ኢያሱ ይሖዋ ባዘዘው መሠረት ለየፎኒ ልጅ ለካሌብ+ በይሁዳ ዘሮች መካከል የምትገኘውን ኬብሮን+ የተባለችውን ቂርያትአርባን ድርሻ አድርጎ ሰጠው (አርባ የኤናቅ አባት ነበር)።

  • ኢያሱ 21:11, 12
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 11 እነሱም በይሁዳ ተራራማ አካባቢ የምትገኘውን ቂርያትአርባን+ (አርባ የኤናቅ አባት ነበር) ይኸውም ኬብሮንን+ እና በዙሪያዋ ያለውን የግጦሽ መሬት ሰጧቸው። 12 ይሁንና የከተማዋን እርሻና መንደሮቿን ለየፎኒ ልጅ ለካሌብ ርስት አድርገው ሰጡት።+

  • 1 ዜና መዋዕል 6:55, 56
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 55 በይሁዳ ምድር የምትገኘውን ኬብሮንን+ በዙሪያዋ ካሉት የግጦሽ መሬቶች ጋር ሰጧቸው። 56 ይሁንና የከተማዋን እርሻና ሰፈሮቿን ለየፎኒ ልጅ ለካሌብ+ ሰጡ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ