ኢያሱ 9:16, 17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 እስራኤላውያንም ከእነሱ ጋር ቃል ኪዳን ከገቡ ከሦስት ቀን በኋላ እነዚህ ሰዎች እዚያው በአቅራቢያቸው የሚኖሩ የአካባቢው ነዋሪዎች መሆናቸውን ሰሙ። 17 ከዚያም እስራኤላውያን ተጉዘው በሦስተኛው ቀን ወደ ከተሞቻቸው ደረሱ፤ ከተሞቻቸውም ገባኦን፣+ ከፊራ፣ በኤሮት እና ቂርያትየአሪም+ ነበሩ። 2 ሳሙኤል 6:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ከዚያም አብሮት ከነበረው ሕዝብ ሁሉ ጋር ተነስቶ የእውነተኛውን አምላክ ታቦት+ ለማምጣት በዙፋን ላይ ከኪሩቤል በላይ የተቀመጠው*+ የሠራዊት ጌታ የይሖዋ+ ስም ወደተጠራበት ወደ በዓለይሁዳ ሄደ። 1 ዜና መዋዕል 13:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ዳዊትና መላው የእስራኤል ሕዝብ ከኪሩቤል በላይ* በዙፋን የሚቀመጠውን+ የእውነተኛውን አምላክ ታቦት ይኸውም ሰዎች የይሖዋን ስም የሚጠሩበትን ታቦት ለማምጣት በይሁዳ ምድር ወደምትገኘው ቂርያትየአሪም ወደምትባለው ወደ ባዓላ+ ወጡ።
16 እስራኤላውያንም ከእነሱ ጋር ቃል ኪዳን ከገቡ ከሦስት ቀን በኋላ እነዚህ ሰዎች እዚያው በአቅራቢያቸው የሚኖሩ የአካባቢው ነዋሪዎች መሆናቸውን ሰሙ። 17 ከዚያም እስራኤላውያን ተጉዘው በሦስተኛው ቀን ወደ ከተሞቻቸው ደረሱ፤ ከተሞቻቸውም ገባኦን፣+ ከፊራ፣ በኤሮት እና ቂርያትየአሪም+ ነበሩ።
2 ከዚያም አብሮት ከነበረው ሕዝብ ሁሉ ጋር ተነስቶ የእውነተኛውን አምላክ ታቦት+ ለማምጣት በዙፋን ላይ ከኪሩቤል በላይ የተቀመጠው*+ የሠራዊት ጌታ የይሖዋ+ ስም ወደተጠራበት ወደ በዓለይሁዳ ሄደ።
6 ዳዊትና መላው የእስራኤል ሕዝብ ከኪሩቤል በላይ* በዙፋን የሚቀመጠውን+ የእውነተኛውን አምላክ ታቦት ይኸውም ሰዎች የይሖዋን ስም የሚጠሩበትን ታቦት ለማምጣት በይሁዳ ምድር ወደምትገኘው ቂርያትየአሪም ወደምትባለው ወደ ባዓላ+ ወጡ።