የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘፀአት 25:22
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 22 እኔም በዚያ እገለጥልሃለሁ፤ ከመክደኛውም በላይ ሆኜ አነጋግርሃለሁ።+ በምሥክሩ ታቦት ላይ በሚገኙት በሁለቱ ኪሩቦች መካከል ሆኜ እስራኤላውያንን በተመለከተ የማዝህንም ሁሉ አሳውቅሃለሁ።

  • 1 ሳሙኤል 4:4
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 4 በመሆኑም ሕዝቡ ሰዎችን ወደ ሴሎ ላከ፤ እነሱም ከኪሩቤል በላይ* ዙፋን ላይ የተቀመጠውን+ የሠራዊት ጌታ የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት ከዚያ ተሸክመው መጡ። ሁለቱ የኤሊ ልጆች ሆፍኒ እና ፊንሃስም+ ከእውነተኛው አምላክ የቃል ኪዳን ታቦት ጋር አብረው ነበሩ።

  • 1 ዜና መዋዕል 13:6-11
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 6 ዳዊትና መላው የእስራኤል ሕዝብ ከኪሩቤል በላይ* በዙፋን የሚቀመጠውን+ የእውነተኛውን አምላክ ታቦት ይኸውም ሰዎች የይሖዋን ስም የሚጠሩበትን ታቦት ለማምጣት በይሁዳ ምድር ወደምትገኘው ቂርያትየአሪም ወደምትባለው ወደ ባዓላ+ ወጡ። 7 ይሁን እንጂ የእውነተኛውን አምላክ ታቦት በአዲስ ሠረገላ ላይ ጭነው+ ከአቢናዳብ ቤት አመጡት፤ ደግሞም ዖዛና አሂዮ ሠረገላውን እየነዱ ነበር።+ 8 ዳዊትና መላው የእስራኤል ሕዝብ በመዝሙር፣ በበገና፣ በባለ አውታር መሣሪያዎች፣ በአታሞ፣+ በሲምባልና*+ በመለከት+ ታጅበው በሙሉ ኃይላቸው በእውነተኛው አምላክ ፊት በደስታ ይጨፍሩ ነበር። 9 ወደ ኪዶን አውድማ ሲደርሱ ግን ከብቶቹ ታቦቱን ሊጥሉት ተቃርበው ስለነበር ዖዛ እጁን ዘርግቶ ታቦቱን ያዘ። 10 በዚህ ጊዜ የይሖዋ ቁጣ በዖዛ ላይ ነደደ፤ ታቦቱን ለመያዝ እጁን በመዘርጋቱም ቀሰፈው፤+ እሱም በአምላክ ፊት እዚያው ሞተ።+ 11 ሆኖም የይሖዋ ቁጣ በዖዛ ላይ ስለነደደ ዳዊት ተበሳጨ፤* ያም ቦታ እስከ ዛሬ ድረስ ጴሬዝዖዛ* ተብሎ ይጠራል።

  • መዝሙር 80:1
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 80 ዮሴፍን እንደ መንጋ የምትመራ

      የእስራኤል እረኛ ሆይ፣+ አዳምጥ።

      ከኪሩቤል በላይ* በዙፋን የምትቀመጥ ሆይ፣+

      ብርሃን አብራ።*

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ