ኢያሱ 16:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 ሆኖም በጌዜር+ ይኖሩ የነበሩትን ከነአናውያን አላባረሯቸውም፤ ከነአናውያንም እስከ ዛሬ ድረስ በኤፍሬም መካከል ይኖራሉ፤+ የግዳጅ ሥራ የመሥራት ግዴታም ተጥሎባቸዋል።+ መሳፍንት 1:30 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 30 ዛብሎንም የቂትሮንን ነዋሪዎችና የናሃሎልን+ ነዋሪዎች አላባረራቸውም። ከነአናውያን አብረዋቸው ይኖሩ የነበረ ሲሆን የግዳጅ ሥራም እንዲሠሩ ተገደው ነበር።+ 2 ዜና መዋዕል 8:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ይኸውም እስራኤላውያን ፈጽመው ያላጠፏቸውን+ በምድሪቱ ላይ የቀሩትን ዘሮቻቸውን ሰለሞን የግዳጅ ሥራ እንዲሠሩ መለመላቸው፤+ እስከ ዛሬም ድረስ ይሠራሉ።
10 ሆኖም በጌዜር+ ይኖሩ የነበሩትን ከነአናውያን አላባረሯቸውም፤ ከነአናውያንም እስከ ዛሬ ድረስ በኤፍሬም መካከል ይኖራሉ፤+ የግዳጅ ሥራ የመሥራት ግዴታም ተጥሎባቸዋል።+