-
ኢያሱ 7:5አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
5 የጋይ ሰዎችም 36 ሰዎችን ገደሉ፤ ከከተማዋ በር አንስቶ እስከ ሸባሪም* ድረስ በማሳደድ ቁልቁለቱ ላይ መቷቸው። በዚህም የተነሳ የሕዝቡ ልብ ቀለጠ፤ እንደ ውኃም ፈሰሰ።
-
-
ኢያሱ 7:24, 25አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
24 በኋላም ኢያሱና ከእሱ ጋር የነበሩት እስራኤላውያን በሙሉ የዛራን ልጅ አካንን፣+ ብሩን፣ የክብር ልብሱን፣ ጥፍጥፍ ወርቁን፣+ ወንዶች ልጆቹን፣ ሴቶች ልጆቹን፣ በሬውን፣ አህያውን፣ መንጋውን፣ ድንኳኑንና የእሱ የሆነውን ሁሉ ወደ አኮር ሸለቆ*+ አመጡ። 25 ኢያሱም አካንን “መዓት* ያመጣህብን ለምንድን ነው?+ ይሖዋም በዛሬው ዕለት መዓት ያመጣብሃል” አለው። ከዚያም እስራኤላውያን በሙሉ በድንጋይ ወገሩት፤+ በእሳትም አቃጠሏቸው።+ በዚህ መንገድ ሁሉንም በድንጋይ ወግረው ገደሏቸው።
-