ዘፀአት 19:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 የሲና ተራራ ይሖዋ በእሳት ስለወረደበት ዙሪያውን ጨሰ፤+ ጭሱም እንደ እቶን ጭስ እየተትጎለጎለ ይወጣ ነበር፤ ተራራውም ሁሉ በኃይል ተናወጠ።+ ነህምያ 9:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 በሲና ተራራ ላይ ወርደህ+ ከሰማይ አነጋገርካቸው፤+ እንዲሁም የጽድቅ ፍርዶችን፣ የእውነት ሕጎችን፣* መልካም ሥርዓቶችንና ትእዛዛትን ሰጠሃቸው።+