5 ፍልስጤማውያንም 30,000 የጦር ሠረገሎች፣ 6,000 ፈረሰኞችና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ እጅግ ብዙ የሆነ ሠራዊት ይዘው ከእስራኤላውያን ጋር ለመዋጋት ተሰባሰቡ፤+ እነሱም ወጥተው ከቤትአዌን+ በስተ ምሥራቅ በሚክማሽ ሰፈሩ። 6 የእስራኤል ሰዎችም አደጋ እንደተጋረጠባቸው ስላዩ ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ገብተው ነበር፤ በመሆኑም ሕዝቡ በየዋሻው፣ በየጉድጓዱ፣ በየዓለቱ፣ በየጎሬውና በየውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓዱ ውስጥ ተደበቀ።+