-
1 ነገሥት 18:26, 27አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
26 በመሆኑም የተሰጣቸውን ወይፈን ወስደው አዘጋጁ፤ ከጠዋት አንስቶ እስከ እኩለ ቀን ድረስም “ባአል ሆይ፣ መልስልን!” እያሉ የባአልን ስም ጠሩ። ሆኖም ድምፅ የለም፤ የሚመልስም አልነበረም።+ በሠሩትም መሠዊያ ዙሪያ እያነከሱ ዞሩ። 27 እኩለ ቀን ገደማም ኤልያስ እንዲህ በማለት ያፌዝባቸው ጀመር፦ “ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ጩኹ እንጂ! አምላክ እኮ ነው!+ ምናልባት በሐሳብ ተውጦ ይሆናል፤ ወይም ሊጸዳዳ ሄዶ ይሆናል።* አሊያም ደግሞ ተኝቶ ሊሆን ስለሚችል የሚቀሰቅሰው ያስፈልገው ይሆናል!”
-