የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኢሳይያስ 45:20
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 20 ተሰብስባችሁ ኑ።

      እናንተ ከብሔራት ያመለጣችሁ፣ በአንድነት ቅረቡ።+

      የተቀረጹ ምስሎቻቸውን ተሸክመው የሚዞሩም ሆኑ

      ሊያድናቸው ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ+ ምንም እውቀት የላቸውም።

  • ኤርምያስ 10:5
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  5 እነሱ በኪያር እርሻ ውስጥ ለወፍ ማስፈራሪያነት እንደሚተከል ማስፈራርቾ መናገር አይችሉም፤+

      መራመድ ስለማይችሉ ተሸካሚ ያስፈልጋቸዋል።+

      ጉዳት ማድረስም ሆነ

      ምንም ዓይነት መልካም ነገር መሥራት ስለማይችሉ አትፍሯቸው።”+

  • ዳንኤል 5:23
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 23 ይልቁንም በሰማያት ጌታ ላይ ታበይክ፤+ የቤተ መቅደሱንም ዕቃ አስመጣህ።+ ከዚያም አንተና መኳንንትህ እንዲሁም ቁባቶችህና ቅምጦችህ በእነዚህ ዕቃዎች የወይን ጠጅ ጠጣችሁ፤ አንዳች ነገር ማየትም ሆነ መስማት ወይም ማወቅ የማይችሉትን ከብር፣ ከወርቅ፣ ከመዳብ፣ ከብረት፣ ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩ አማልክት አወደሳችሁ።+ እስትንፋስህንና መንገድህን ሁሉ በእጁ የያዘውን አምላክ ግን አላከበርክም።+

  • ዕንባቆም 2:18, 19
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 18 የተቀረጸ ምስል፣

      ሠሪው የቀረጸው ከሆነ ምን ጥቅም አለው?

      ሠሪው እምነት ቢጥልበትም እንኳ

      ከብረት የተሠራ ሐውልትና* ሐሰትን የሚናገር አስተማሪ ምን ፋይዳ አለው?

      መናገር የማይችሉ ከንቱ አማልክት መሥራት ምን እርባና አለው?+

      19 እንጨቱን “ንቃ!”

      መናገር የማይችለውንም ድንጋይ “ተነስ! አስተምረን!” ለሚል ወዮለት!

      እነሆ፣ በወርቅና በብር ተለብጧል፤+

      በውስጡም እስትንፋስ የለም።+

  • 1 ቆሮንቶስ 8:4
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 4 ለጣዖቶች የቀረበ ምግብ መብላትን በተመለከተ፣ በዓለም ላይ ጣዖት ከንቱ እንደሆነና+ ከአንዱ በቀር አምላክ እንደሌለ እናውቃለን።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ