ኢያሱ 19:47, 48 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 47 የዳን ዘሮች ርስታቸው በጣም ጠቧቸው ነበር።+ በመሆኑም ወጥተው ለሸምን+ ወጉ፤ ከተማዋንም በመቆጣጠር በሰይፍ መቷት። ከዚያም ከተማዋን ርስት አድርገው በመያዝ በዚያ መኖር ጀመሩ፤ ለሸምንም በአባታቸው በዳን ስም ዳን ብለው ጠሯት።+ 48 የዳን ነገድ ርስት በየቤተሰቡ ይህ ነበር። ከተሞቹና መንደሮቻቸው እነዚህ ነበሩ። መሳፍንት 18:29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 በተጨማሪም ከተማዋን ለእስራኤል በተወለደለት+ በአባታቸው በዳን ስም ዳን+ ብለው ጠሯት። የከተማዋ የቀድሞ ስም ግን ላይሽ ነበር።+
47 የዳን ዘሮች ርስታቸው በጣም ጠቧቸው ነበር።+ በመሆኑም ወጥተው ለሸምን+ ወጉ፤ ከተማዋንም በመቆጣጠር በሰይፍ መቷት። ከዚያም ከተማዋን ርስት አድርገው በመያዝ በዚያ መኖር ጀመሩ፤ ለሸምንም በአባታቸው በዳን ስም ዳን ብለው ጠሯት።+ 48 የዳን ነገድ ርስት በየቤተሰቡ ይህ ነበር። ከተሞቹና መንደሮቻቸው እነዚህ ነበሩ።