መሳፍንት 3:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ስለዚህ እስራኤላውያን በይሖዋ ፊት መጥፎ ነገር አደረጉ፤ አምላካቸውን ይሖዋንም ረሱ፤ ባአልንና+ የማምለኪያ ግንዶችን* + አገለገሉ። መሳፍንት 10:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 እስራኤላውያንም በይሖዋ ፊት እንደገና መጥፎ ነገር አደረጉ፤+ ባአልን፣+ የአስታሮትን ምስሎች፣ የአራምን* አማልክት፣ የሲዶናን አማልክት፣ የሞዓብን አማልክት፣+ የአሞናውያንን አማልክትና+ የፍልስጤማውያንን አማልክት+ ማገልገል ጀመሩ። ይሖዋን ተዉት፤ እሱንም አላገለገሉም። 1 ነገሥት 11:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ሰለሞን የሲዶናውያንን እንስት አምላክ አስታሮትንና+ አስጸያፊ የሆነውን የአሞናውያንን አምላክ ሚልኮምን+ ተከተለ።
6 እስራኤላውያንም በይሖዋ ፊት እንደገና መጥፎ ነገር አደረጉ፤+ ባአልን፣+ የአስታሮትን ምስሎች፣ የአራምን* አማልክት፣ የሲዶናን አማልክት፣ የሞዓብን አማልክት፣+ የአሞናውያንን አማልክትና+ የፍልስጤማውያንን አማልክት+ ማገልገል ጀመሩ። ይሖዋን ተዉት፤ እሱንም አላገለገሉም።