ዘፀአት 23:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 “ጉቦ አትቀበል፤ ምክንያቱም ጉቦ አጥርተው የሚያዩ ሰዎችን ዓይን ያሳውራል፤ እንዲሁም የጻድቅ ሰዎችን ቃል ሊያዛባ ይችላል።+ ዘዳግም 16:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 ፍርድን አታዛባ፤+ አድልዎ አትፈጽም+ ወይም ጉቦ አትቀበል፤ ምክንያቱም ጉቦ የጥበበኞችን ዓይን ያሳውራል፤+ የጻድቃንንም ቃል ያጣምማል። መዝሙር 15:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ገንዘቡን በወለድ አያበድርም፤+ንጹሕ የሆነውን ሰው ለመወንጀልም ጉቦ አይቀበልም።+ እነዚህን ነገሮች የሚያደርግ ሰው ሁሉ ፈጽሞ አይናወጥም።*+ ምሳሌ 29:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ንጉሥ ፍትሕ በማስፈን አገርን ያረጋጋል፤+ጉቦ የሚፈልግ ሰው ግን ያወድማታል።