ዘፀአት 15:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 ይሖዋ ሆይ፣ ከአማልክት መካከል እንደ አንተ ያለ ማን ነው?+ በቅድስናው ኃያል መሆኑን የሚያሳይ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?+ በመዝሙር ልትወደስ የሚገባህ የምትፈራ አምላክ ነህ፤ ድንቅ ነገሮችን ታደርጋለህ።+ ዘዳግም 4:35 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 35 እውነተኛው አምላክ፣ ይሖዋ መሆኑን ታውቅ ዘንድ እነዚህን ነገሮች እንድታይ ተደርገሃል፤+ ከእሱ ሌላ ማንም የለም።+ መዝሙር 73:25 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 25 በሰማይ ማን አለኝ? በምድርም ላይ ከአንተ ሌላ የምሻው የለም።+ መዝሙር 86:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ይሖዋ ሆይ፣ ከአማልክት መካከል እንደ አንተ ያለ የለም፤+ከአንተ ሥራ ጋር የሚወዳደር አንድም ሥራ የለም።+ መዝሙር 89:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 በሰማያት ከይሖዋ ጋር ማን ሊወዳደር ይችላል?+ ከአምላክ ልጆች*+ መካከል እንደ ይሖዋ ያለ ማን ነው?
11 ይሖዋ ሆይ፣ ከአማልክት መካከል እንደ አንተ ያለ ማን ነው?+ በቅድስናው ኃያል መሆኑን የሚያሳይ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?+ በመዝሙር ልትወደስ የሚገባህ የምትፈራ አምላክ ነህ፤ ድንቅ ነገሮችን ታደርጋለህ።+